የፌዴራል መንግሥቱ ለቤት ውስጥ አመፅ ሰለባዎች ድጋፍ መኖሩን የሚገልጥ አዲስ ዘመቻ ጀመረ

** የርቀትና የክፍል ውስጥ ትምህርት መንግሥትንና ሌበር ፓርቲን አወዛገበ

1600 Core bulletin 3 May 2020

Source: SBS

ቫይረስ - የቤት ውስጥ አመፅ

 

 የፌዴራል መንግሥቱ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ለቤተሰብ አመፅ ተጠቂዎች ድጋፍ መኖሩን የሚያሳስብ አዲስ ዘመቻ ጀመረ።

'እገዛ እዚህ አለ' በሚል ማስታወቂያ በሚዲያና የሕክምና ሥፍራዎች የቤት ውስጥ አመፅ ተጠቂዎች እርዳታ እንዲጠይቁ ልብ እያሰኘ ነው።  

ዘመቻው በአሁኑ ወቅት ያሉ ግልጋሎትችንና የቀጥታ ስልክ ቁጥሮችን አካትቷል። እርዳታ ፈላጊዎች 1800RESPECT [[1800 737 732]] እንዲሁም MensLine Australia ዘንድ [[1300 78 99 78]] መደወል ይችላሉ።

የቤተሰቦች ሚኒስትር አን ራስቶን ምንም እንኳ አውስትራሊያውያን ከፍ ያለ የመንፈስ ሁከት ገጥሟቸው ያለ ቢሆንም፤ ሌሎች ላይ ጥቃት ለመፈጸም ግና ይቅር የሚያሰኝ እንዳልሆነ ሲያስገነዘቡ፤

"ሁሉም ሰው የመንፈስ መታወክ ቢገጥመውም፤ በተለይ ግና በቤት ውስጥ አመፅ ውስጥ ላሉቱ እጅጉን አዋኪ ነው። እኛ የምንልው ምንድነው፤ ወቅቱ የፈለገውን ያህል አዋኪም ቢሆን በሌላው ላይ ጥቃትን መሰንዘር ይቅር አያሰኝም" ብለዋል።   

                                         

 

ቫይረስ - ትምህርት ቤቶች

 የሌበር ፓርቲ - ቤተሰቦች የተቻላቸውን ያህል የርቀት ትምህርት ክትትልን እየተወጡ ባሉበት ሁኔታ ዝንቅ መልዕክቶችን ማስተላለፍ አግባብ እንዳልሆነ አሳሰበ።

 የፌዴራል ትምህርት ሚኒስትር ዳን ቲሃን የቪክቶሪያ መንግሥት አያሌ ተማሪዎች የርቀት ትምህርትን እንዲከታተሉ ብርቱ ተፅዕኖ አሳድሯል ሲሉ ከሰዋል።

ቪክቶሪያ ከሌሎች ስቴቶች ለየት ባለ መልኩ እስከ ሜይ 11 የተጣለው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እስኪያበቃ የርቀት ትምህርት እንዲቀጥልና ከዚያ በኋላ ላሉት ጊዜያት ክለሳ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

 የፌዴራል ሌበር የትምህርት ቃል አቀባይ ታኒያ ፕሊበርስክ የሚኒስትር ዳን ቲሃን ጣልቃ ገብነት ገንቢ እንዳልሆነ ሲያመላክቱ፤  

 

"ወላጆች ሊያደምጡ የሚገባው የየስቴታቸውን ፕሪሚየሮች ነው። በእያንዳንዳንዱ የአውስትራሊያ ክፍል፤ ስቴቶች ወላጆች ወደ ሥራ መሰማራት ካለባቸው ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት መስደድ እንደሚችሉ ግልጽ አድርገዋል። እንዲሁም፤ ልጆቻቸው በትምህርት ወደ ኋላ የቀሩ ከሆነ ወደ ትምህርት ቤት መላክ ይችላሉ። ከዚያ ባሻገር የፌዴራል ሚኒስትሩ የስቴት የትምህርት ሚኒስትሮችንና ፕሪሚየሮችን እንዲያውኩ አንሻም" በማለት የፊዴራል መንግሥቱ በስቴት የትምህርት አመራር ውስጥ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠብ አሳስበዋል።

አቶ ቲሃን በቪክቶሪያ ትምህርት ቤቶች ጉዳይ ጣልቃ የገቡትና ፕሪሚየሩ ላይም ትችት የሰነዘሩት በብስጭት ሳቢያ እንደሆነና ያም መስመር ያለፈ በመሆኑ የሰነዘሯቸውን ትችቶች መልሰው ማንሳታቸውን አስታውቀዋል።    

                                    

 

ኢሚግሬሽን

 የፌዴራል ተቃዋሚ ቡድን ወደ አውስትራሊያ የሚገቡ ጊዜያዊ የውጭ ሠራተኞች ቁጥር ላይ ቅነሳ እንዲደረግ አስገነዘበ።

የሌበር ኢሚግሬሽን ሚኒስትር ክሪስቲና ኬኔሊ ባለፈው ዓመት አጋማሽ ላይ አውስትራሊያ ውስጥ ከሁለት ሚሊየን በላይ የጊዜያዊ ቪዛ ተጠቃሚዎች እንደነበሩ ጠቅሰው፤ የአውስትራሊያ ዜጎችና ነዋሪዎች መጤዎች ባለፉት ቅርብ ዓመታት ውስጥ ሲሠሯቸው የነበሩ ዓይነት ሥራዎችን ሊሠሩ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

 

 

                                                             

 


Share

Published

Updated

By NACA
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends