ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት ሐሙስ 723 በኮሮናቫይረስ ሲጠቁባት 13 ሰዎቿም ሕይወታቸውን አጥተውባታል። ይህም በእጅጉ ከፍተኛው ቁጥር ነው።
ሰኞ ዕለት ቪክቶሪያ ውስጥ በአንድ ነጠላ ቀን ከፍተኛ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 532 ነበር።
ማክሰኞ ቁጥሩ ወደ 384 ሲወርድ ረቡዕ ወደ 295 አሽቆልቁሎ ነበር።
የቪክቶሪያ ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ በአሁኑ ወቅት በሪጂናል ቪክቶሪያ 255 የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች መኖራቸውን ገልጠዋል።
ይህንኑም ተከትሎ ማናቸውም የሪጂናል አውስትራሊያ ነዋሪ የሆኑ በሙሉ ከእሑድ 11:59 pm ጀምሮ ከቤታቸው ሲወጡ ጭምብል የማጥለቅ ግዴታ እንዳለባቸው ፕሪሚየር አንድሩስ በዛሬው ዕለት አስታውቀዋል።
በዚህም መሠረት መላው የቪክቶሪያ ነዋሪዎች ከቤታቸው ሲወጡ ጭምብል ሳያጠልቁ መንቀሳቀስ አይችሉም።
እንዲሁም፤ የ Greater Geelong, Surf Coast, Moorabool, Golden Plains, Colac-Otway እና Queenscliff ነዋሪዎች ከሐሙስ 11:59pm ጀምሮ ቤታቸው ውስጥ እንግዳ ተቀብለው ማስተናገድ አይፈቀድላቸውም።