የአዕምሮ ጤና ሕክምናን ማግኘት

አንዳንዴ የመንፈስ ጭንቀትና መረበሽ የዕለት - ተዕለት ሕይወታችን ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ጉዳዮች ይሆናሉ። 'ጤናማ' እና የባለሙያ እርዳታ የሚያስፈልግ የመሆን ፍንጭን እንደምን ማወቅ ይችላሉ? የእርስዎ ጠቅላላ ሐኪም በአዕምሮ ጤና ሕክምና ዕቅድ ነደፋ አኳያ ሊያግዝዎት ይችላል።

woman on bed with hands over eyes

Source: Getty Images/Tara Moore

እንደ ብሔራዊ የአዕምሮ ጤናና ደኅንነት የዳሰሳ ጥናት በ2017-18 ከአምስት አንድ አውስትራሊያውያን (20% ወይም 4.8 ሚሊየን) በሕይወት ዘመናቸው ውስጥ ብርቱ የሆኑ የአዕምሮ ጤና ጉዳዮች ገጥሟቸዋል።

ሩብ ሚሊየን ያህሉም የባሕላዊና ቋንቋዊ ዝንቅነት መደብ ጀርባ ያላቸው የመጀመሪያ - ትውልድ አውስትራሊያውያን ናቸው። 

ምንም እንኳ በአሁኑ ወቅት ከፍ ያለ የአዕምሮ ጤና ጉዳዮች ግንዛቤ ቢኖርም፤ ዛሬም ድረስ በርካታ ሰዎች እርዳታ ለመጠየቅ የማይዳዱ አሉ። 


 

አንኳሮች፡

  • የፌዴራል መንግሥቱን የጤና ክብካቤ ግልጋሎቶች በ Primary Health Networks (PHN) እና Better Access initiative (BAI) አማካይነት ማግኘት ይችላሉ። 
  • የአዕምሮ ጤና ዕቅድ የሚጀምረው ከጠቅላላ ሐኪም ዘንድ ነው
  • አስቸኳይ ድጋፍ በ Beyond Blue ድረ - ገጽ በኩል ይገኛል

የፌዴራል መንግሥቱን የአዕምሮ ጤና ግልጋሎቶች ለማግኘት ሁለት መንገዶች አሉ።

  1. The Primary Health Networks (ቀዳሚ የጤና አውታረ መረቦች)
  2. The Better Access initiative (የተሻለ መዳረሻ ተነሳሽነት) በኩል የሥነ አዕምሮ፣ ሥነ ልቦናና ጠቅላላ ሐኪሞችን ማግኝት
በሪጂናል ደረጃ የፌዴራል መንግሥቱ ለአዕምሮ ጤናና ራስን በራስ ማጥፋት ቅድመ መከላከል የሚውል ድጎማ ለቀዳሚ የጤና አውታረ መረቦች (PHN) ይደጉማል።

 የተሻለ መዳረሻ ተነሳሽነት (BAI) በሜዲኬይር አማካኝነት የሚደገፍ ሲሆን የታቀደውም ማኅበረሰብ ውስጥ ያለውን የአዕምሮ ጤና ሕክምናና አስተዳደር ለማሽሻል ነው።

በሜልበርን ዩኒቨርሲቲ - የሉላዊና ባሕላዊ ጤና ክፍል ዋና ኃላፊ የሆኑት ፕሮፌሰር ሃሪ ሚናስ ለእያንዳንዱ ዕርዳታ ጠያቂ የመጀመሪያ መነሻ ሥፍራ ጠቅላላ ሐኪሞች መሆን አለባቸው ይላሉ።

እንዲሁም፤ የባሕላዊና ሃይማኖታዊ እምነቶች ሰዎችን የአዕምሮ ጤና እርዳታ ከመጠየቅ እንዲገቱ ጋሬጣ እንደሚሆኑባቸው የሚረዱ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።
ከአዕምሮ ጤና ጋር የሚያያዘው የመገለልና ሐፍረት ደረጃ በጣሙን ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል።
በፌዴራል መንግሥቱ የባሕላዊና ቋንቋዊ ዝንቅ የመደብ ጀርባ ላላቸው ሰዎች የአዕምሮ ጤና የቀረጸው ፕሮግራም መድብለ- ባሕላዊት አውስትራሊያ ይባላል። 

በተጨማሪም ወደ አውስትራሊያ ከመምጣታቸው በፊት አካላዊና መንፈሳዊ ሰቆቃ የደረሰባቸውን ሰዎች ለመርዳት የተለየ ፕሮግራም አለ። 
mental health, young man, anxiety
Young man sitting at kitchen table with hands on face Source: Getty Images/Aleli Dezmen
በአውስትራሊያን የተወሳሰበ የጤና ክብካቤ ሥርዓት ውስጥ ለማለፍ ለሰዎች አዋኪ እንደሚሆንም ፕሮፌሰር ሚናስ ጠቁመዋል።

አክለውም፤ ጠቅላላ ሐኪሞች እገዛ ለማድረግ ዝግጁ ስለመሆናቸውና እንደ መንፈስ ጭንቀትና መረበሽ ላሉት የአዕምሮ ጤናን ዕውክታዎች የሕክምና እርዳታ ለማድረግ መልካም ስልጠና እንዳላቸው ተናግረዋል።
ጠቅላላ ሐኪምዎ የእርስዎ የመጀመሪያ የግንኙነት መነሻ ነው።
የአዕምሮ ጤና ሕክምና ዕቅድ ለመንደፍ መነሻዎቹ እርስዎ ምን ዓይነት ስሜት እንደሚሰማዎ ከመነጋገር ነው።

እርስዎና ጠቅላላ ሐኪምዎ ባለፉት አራት ሳምንታት ውስጥ ምን ዓይነት የመንፈስ ጭንቀትና መረበሽ ተሰምቶዎት እንደነበር ለመገምገምና ለመረዳት የሚያስችል ቀላል ዝርዝር ጉዳዮች ማስፈሪያ አለ።

የእርስዎ ጠቅላላ ሐኪም ወደ ስፔሽያሊስት ለመመራት ምን እንደሚሰማዎት ለማገዝ ዝርዝሩን ጉዳዮቹን በማስፈሩ ረገድ ይረዳዎታል።
የሥነ አዕምሮ ሐኪም ለማየትና የሚዲኬይር ተመላሽ ገንዘብ ለማግኘት በጠቅላላ ሐኪም ወደዚያ መመራትን ግድ ይላል።
ሜዲኬይር ካርድ ካለዎት በአንድ የዘመን መቁጠሪያ ዓመት ለ10 የግል ወይም የቡድን ጊዜያት የሥነ አዕምሮ ሐኪም፣ ማኅበራዊ ሠራተኛ ወይም የሥራ መስክ አካሚን መጎብኘትይችላሉ። እያንዳንዱ ጉብኝትዎ በሜዲኬይር የሚሸፈን ቢሆንም፤ በእያንዳንዱ ጉብኝትዎ የተወሰነ ክፍያ እንደሚኖረው ልብ ሊሉ ይገባል። አካሚዎችዎ እንደማንኛውም የሕክምና ስፔሺያሊስት የራሳቸው የሆነ የሕክምና ክፍያዎች አሏቸው።

በአንድ የዘመን መቁጠሪያ ዓመት ከ10 ጊዜ በላይ ስፔሻሊስቶች ዘንድ መቅረብ የሚያስፈልግዎት ከሆነ፤ የጠቅላላ ሐኪምዎ በቀዳሚ የጤና አውታረ መረቦች (PHN) ዕቅድ በኩል ግልጋሎት የሚያገኙበትን ምክረ ሃሳብ ይሰጥዎታል።
mental health, senior patient, doctor counselling
Doctor consoling sad senior male patient Source: Getty Images
በገጠርና ዳርቻ አካባቢዎች ላሉ ሰዎች፤ የተሻለ መዳረሻ ተነሳሽነት (BAI) የአዕምሮ ጤና ግልጋሎቶችን በቪዲዮ ኮንፈረንስ እንዲያገኙ ያመቻችልዎታል።

እንደ ፕሮፌሰር ሚናስ ገለጣ፤ አነስተኛ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ ያለ ጠቅላላ ሐኪም አስተላላፊነት በቀጥታ የአዕምሮ ጤና ማዕከላትን የማግኛ ቀላሉ መንገድ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ነው።
በቀጥታ ወደ ማኅበረሰብ የአዕምሮ ጤና ማዕከል መሔድ ይችላሉ።
አስቸኳይ እርዳታ የሚሹ ከሆነ ለመላው ስቴትና ግዛቶች የ Beyond Blue ድረገጽ መረጃዎችን ይሰጣል።

ከድረገጹም ማንነትዎን የማይገልጥ የስልክ ንግግር፣ የጽሑፍ ልውውጥ ወይም በኢሜይል በአዕምሮ ጤና ከሰለጠነ ባለሙያ መረጃና ምክርን ማግኘት ይችላሉ።

እንግሊዝኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎ ካልሆነና አስተርጓሚ የሚሹ ከሆነ በትርጉምና አስተርጓሚ ግልጋሎት በኩል ነጻ ግልጋሎት ማግኘት ይችላሉ።

ሜዲኬይር ካርድ ባይኖሮዎትም እንኳ የ Beyond Blue ግልጋሎትን ማግኘት ይችላሉ።
Online consultation, female doctor, Asian doctor
Online consultation with a female doctor of Asian background Source: Getty Images/Kilito Chan
ስለ የአዕምሮ ጤና ተነሳሽነት ተጨማሪ መረጃ ካሹ   ድረገጽን ይጎብኙ።
የሥነ ልቦና ሐኪሞች ዝርዝር ማውጫ ከፈለጉ  ድረገጽን ይጎብኙ።
እርዳታ ወይም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት  ድረገጽን ይጎብኙ።


Share
Published 28 May 2020 3:29pm
Updated 28 May 2020 7:07pm
By Josipa Kosanovic
Presented by Kassahun Seboqa Negewo


Share this with family and friends