በመላው አውስትራሊያ ክፍለ አገራትና ግዛቶች ባለው ከፍተኛ የክትባት መጠን አስባብ የዓለም አቀፍ ጉዞ መቀጠልና የተጣሉ ገደቦች መነሳት ታይተዋል።
በሳቢያውም በቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር እንደሚያሻቅብ ይጠበቃል፤ የኦሚክሮንና ዴልታ ቫይረሶች እጅግ ተዛማችነትን ተከትሎም የጤና ባለ ስልጣናት ሰዎች ብርቱ መከላከያ እንዲሆናቸው ተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባቶችን እንዲከተቡ ጥሪዎችን እያቀረቡ ነው።
የክትባት ቴክኖሎጂ የተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባቶች ምልከታ ከቀድሞዎቹ የመጀመሪያና ሁለተኛ ክትባቶች ጋር ተመሳሳይ መሆንን አበክሮ ያመለክታል .
“ተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባት በተለይም በመላው ዓለም ሊስፋፋ ስለሚችለው ኦሚክሮን ቫይረስ ታካይ መከላከያነት በጣሙን አስፈላጊ ነው" ሲሉ የጤና ዲፓርትመንት ፀሐፊ ብሬንዳን መርፊ ወርኃ ዴሴምበር ውስጥ ተናግረዋል።
የተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባት ዘመቻዎች
የፌዴራል ጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት ዴሴምበር መጀመሪያ ላይ የበዓል ሰሞን ከመጀመሩ በፊት አገር አቀፍ የተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባት ዘመቻን አስጀምረዋል፤ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ሰዎች የኦሚክሮን ቫይረስን ለመከላከል ካላቸው ውስን የመከላከል አቅም አስጊነት ጋር ተያይዞ አውስትራሊያውያን በተቻለ መጠን ፈጥነው እንዲከተቡም ማሳሳቢያ ተሰጥቶባቸዋል።
በሳቢያውም የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን ከዋነኛ ክትባት በኋላ የተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባት መከተቢያ ተመካሪ ጊዜን ከስድስት ወራት ወደ አምስት ወራት ቀደም እንዲል አድርጓል
እስከ 1.5 ሚሊየን አውስትራሊያውያን አሁኑኑ የተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባትን መከተብ ይችላሉ።
የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን ከፋይዘር በተጨማሪ የሞደርና ክትባትንም በተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባትነት ግልጋሎት ላይ እንዲውል ይሁንታውን ቸሯል
ተሳትፎን ለማበረታታት የፌዴራልና ክፍለ አገራዊ መንግሥታት የተለያዩ የተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባት ዘመቻዎችን በመላ አገሪቱ ያካሂዳሉ
ተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባቶች ለአረጋውያን
እንደ መንግሥት አማካሪ አባባል ዕድሜያቸው በ70ዎቹና ከዚያ በላይ ያለ አረጋውያን፣ ዕድሜያቸው 65 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ስር የሰደደ ሕመም ያለባቸው፣ በሽታን የመከላከል አቅማቸው ደካማ የሆነ፣ የአቦርጅናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ሆነው ዕድሜያቸው 50 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ስር የሰደደ ሕመም ያለባቸው ሰዎች ለኮሮናቫይረስ ከተጋለጡ ለብርቱ ሕመም ለመዳረግ ተጋላጭ ናቸው።
የፌዴራል ጤና ዲፓርትመንት ስታቲስቲክስ እንደሚያመለክተው ከጃኑዋሪ 2020 ወዲህ 1,910 አረጋውያን አውስትራሊያውያን በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል።
በተለይም ለዴልታና ኦሚክሮን ተላላፊነት የተጋላጭነት መጠን ከፍተኛ ነው፤ ክትባት ለብርቱ ሕመም ወይም ለሞት ተጋላጭነትን በእጅጉ ዝቅ ያደርጋል።

PM Scott Morrison received his COVID-19 booster vaccination alongside Jane Malysiak in NSW. Source: SMH POOL
በአገር አቀፉ ተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባት ቀዳሚ ተከታቢ የሆኑት አረጋውያን አውስትራሊያን ናቸው።
ዕድሚያቸው 18 እና ከዚያም በላይ የሆነ አውስትራሊያውያን ለመደበኛውም ሆነ ተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባትን ለመከተብ የመንግሥትን የክትባት መመዘኛ የሚያሟሉ ናቸው
በአረጋውያን የክብካቤ ተቋማት ያሉ አረጋውያን ቀዳሚውንም ሆነ ተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባቶችን በጋራ ብልፅግናው ክሊኒኮች ሊከተቡ ይችላሉ።
የክብካቤ ተቋማቱ የክትባት ቀነ ቀጠሮን አስመልክቶ ከአረጋውያኑ ወይም የእነሱ ተለዋጭ ውሳኔ ሰጪዎች ጋር መወያየት ይችላሉ።
ክትባት ለልጆች
የፈዋሽ ቁሶች አስተዳደርና የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን ዕድሜያቸው ከአምስት እስከ 11 ላሉ ልጆች ለፋይዘር ክትባት ጊዜያዊ ይሁንታን ሰጥተዋል
ይሁንታው የተሰጠው በቅርብ የተካሄዱ ክሊኒካዊ የሙከራ ውጤቶች እንዳመለከቱት ክትባቱ ከፍተኛ ፍቱንነትን ያሳየና አብዛኛዎቹ የጎንዮሽ ጉዳቶች መለስተኛና ጊዜያዊ በመሆናቸው እንደሆነ የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ለዚህ ክትባት ቀነ ቀጠሮ ለማስያስያዝ የሚቻል ሲሆን ክትባቱን መከተብ የሚጀምረው ግና ከጃኑዋሪ 10, 2022 ጀምሮ ነው።
ክትባቶቹን ከጠቅላላ ሐኪሞች፣ የአቦርጂናል ጤና አገልግሎቶች፣ የማኅበረሰብ መድኃኒት ቤቶችና የክፍለ አገርና ግዛት ክሊኒኮች ዘንድ መከተብ ይቻላል።

Vaccinating children can help reduce community transmission and prevent them passing the virus onto the wider community. Source: Getty Images
ዕድሜያቸው ከአምስት እስከ 11 ያሉና ለብርቱ ሕመሞች ተጋላጭ ሆነው ያሉ፣ የአቦርጅናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሕፃናትና በተፋፈገ ሁኔታዎች ውስጥ የሚኖሩ ወይም ወረርሽኑ በተዛመተበት አካባቢ ያሉ ከብርቱ ተጋላጭነትነታቸው አኳያ ከኮቪድ-19 ክትባት በጣሙን ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን አመልክቷል።
በእንዚህ ዕድሜ ክልል ያሉ ሆነው ቀደም ሲል በኮቪድ -19 ተጠቅተው የነበሩ ሕፃናት ከሕመማቸው ካገገሙ በኋላ መከተብ ይችላሉ።
ለልጆች እንዲሰት ምክረ ሃሳብ የተቸረበት የክትባት መጠን ከአዋቂዎች ለየት ይላል፤ ዕድሜያቸው 12 እናን ከዚያ በላይ ላሉ የሚሰጠው የክትባት መጠን 30 ማይክሮግራምስ ሲሆን ለልጆች የሚሰተው 10 ማይክሮግራምስ ይሆናል።
የመጀመሪያ ክትባታቸውን ከተከተቡ በኋላ ወደ 12 ዓመት ከፍ ያሉ ልጆች ቀጣዩን ሙሉ ክትባት የሚከተቡት አዋቂዎች የሚከተቡትን የፋይዘር ኮቪድ-19 ክትባት ይሆናል።
ተጨማሪ እርዳታን ማግኘት የምችለው ከየት ነው?
በዓለም የጤና ድርጅት ኦሚክሮን በ 'አሳስቢ ቫሪያንት' ከተፈረጀ በኋላ የፌዴራል መንግሥቱ ስለ ተጨማሪ ማጠናከሪያ ክትባት ግንዛቤ ለማስጨበጥ ጥረቶቹን አድሷል።

Booster doses provide an added layer of protection. Source: AAPAAP Image/Bianca De Marchi
"አለመታደል ሆኖ፤ ኮቪድ-19ኝን አስመልክቶ የጎንዮሽ ጉዳት አልባ ሕክምና የለም" ብለዋል።
ተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባትን ከሁለተኛ ክትባት አምስተኛ ወራት በኋላ መከተብ ይቻላል፤ የሁለተኛ ክትባት ቀንም የተከታቢው ግለሰብ ዲጂታል የምስክር ወረቀት ላይ ሰፍሮ ይገኛል።
ስለ ኮቪድ-19 መረጃን በቋንቋዎ በአስተርጓሚ በኩል ለማግኘት በ ድረገጽ በኩል ወይም 1800 131 450 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ስለ ኮቪድ-19 ክትባትና ቀነ ቀጠሮ ማስያዝን አስመልክቶ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፤ የብሔራዊ ኮሮናቫይረስ ቀጥታ መስመርን 1800 020 080 ይደውሉ።
ስለ ኮቪድ-19 ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከሐኪምዎ ወይም የጤና ባለሙያ ጋር እንዲነጋገሩ ይመከራል።