ለመላው ዓለም የአውስትራሊያ ዓመታዊው የአዲስ ት ቅበላ ትዕይንት ገፅታ በሆነቸው ሲድኒ ወደብ ድልድይና ኦፕራ ሃውስ ዙሪያ በተንጣለለው ውቅያኖስ ላይ ትናንት እኩለ ለሊት በተከናወነው ርችት ተኩስና የመዝናኛ ዝግጅቶች ላይ አንድ ሚሊየን ያህል ነዋሪዎችና ቱሪስቶች ታድመዋል።
የኒው ሳውዝ ዌይልስ ፖሊስ ባወጣው መግለጫው ከጥቂቶች በስተቀር አያሌ ሰዎች በዓሉን በመልካም ሁኔታ ተደስተው እንዳሳለፉ ገልጧል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዝም ለመላው አውስትራሊያውያን የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ከወረርሽኙ ወዲህ ሜልበርን ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሔደው የአዲስ ዓመት ቅበላ ላይ 450,000 ነዋሪዎች ታድመው አራት ሚሊየን ዶላር የፈጀውን የርችት ተኩስ ተመልክተዋል።
![NYE 2022 Melbourne.jpg](https://images.sbs.com.au/ac/7f/e81fd2514a08a10636d88f4054a8/nye-2022-melbourne.jpg?imwidth=1280)
The 9pm fireworks on New Year's Eve 2022 featured pylon projections honouring the knowledge and resilience of Aboriginal people. The display also used the motifs of sky, land and sea. Credit: Supplied / Morris McLennan/City of Sydney
በአውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማሕበረሰብ አባላትን ጨምሮ በርካታ አውስትራሊያውያን መጪው 2023 ከፍ ያለ መልካም ነገሮችን ይዞ እንድሚመጣ ያላቸውን ተስፋ እየገለጡ ነው።