ከሉላዊው የፋይናንስ ቀውስ ወዲህ አውስትራሊያን ግዙፍ የቤት ዋጋ ማሽቆልቆል ገጥሟታል፤ አስባቡ ምንድን ነው?

የአውስትራሊያ የቤት ዋጋዎች ቅነሳ ከ2008ቱ ሉላዊ የፋይናንስ ቀውስ ወዲህ በአማካይ በአገር አቀፍ ደረጃ የ 6.4 ፐርሰንት ዓመታዊ ማሽቆልቆልን አሳይቷል።

Newly built houses in the Denham Court suburb of Sydney, Australia, on Tuesday, May 3, 2022.jpg

Newly built houses in the Denham Court suburb of Sydney, Australia, on Tuesday, May 3, 2022. Credit: Brendon Thorne/Bloomberg via Getty Images

አንኳሮች
  • ዓመታዊው የቤት ዋጋዎች ማሽቆልቆል ከሉላዊው የፋይናንስ ቀውስ ወዲህ ግዙፉ ሆኗል
  • ዓመታዊው የቤት ዋጋ ቅነሳ በአማካይ 5.3 ፐርሰንት ወርዷል
  • በተመሳሳይ ጊዜ የቤት ኪራይ በአገር አቀፍ ደረጃ በአማካይ 10.2 ፐርሰንት አሻቅቧል
አውስትራሊያ ውስጥ የቤት ዋጋ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ተከታታይ የብድር ወለድ ጭማሪን ተከትሎ አሽቆልቁሏል።

ሎጂክ ዳታ እንዳመለከተው በወርኃ ዲሴምበር በ 1.1 ያዘቀዘቀ ሲሆን፤ በ12 ወራት ውስጥ በጥቅሉ በ 5.3 ፐርሰንት ወርዷል።

በሌላ በኩል ግና በአገር አቀፍ ደረጃ የቤት ኪራይ ዋጋ ባለፈው ዓመት በአማካይ በ 10.2 ፐርሰንት አሻቅቧል።

የቤት ዋጋ የማሽቆልቆል አስባቦች ምንድን ናቸው? ማሽቆልቆሉስ ይቀጥላልን?

እንደ ኮርሎጂክ የቤቶች ተንታኛዋ ኢሊዛ ኦዌን አባባል አሁነኛ አስባቡ የአውስትራሊያ ብሔራዊ ባንክ በተከታታይ በጣላቸው የብድር ወለዶች ሳቢያ የብድር ወለድ መጠን 3.1 ፐርሰንት መድረሱ ነው።

ኦዌል፤ ማዕከላዊ ባንኩ በዚህም ዓመት የወለድ መጠኑን በመጨመሩ ከቀጠለ የቤት ዋጋም ያንኑ ተከትሎ መውረዱን እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

ይሁንና የብድር ወለድ መጠኑ በዚህ ዓመት አጋማሽ ላይ ከፍተኛው ጫፍ ላይ ደrሶ መገታት ከቻለ ለቤት ባለቤቶች መልካም ዜና እንደሚሆንም አመላክተዋል።

በሌላም በኩል የፕሮፕትራክ የምጣኔ ሃብት ተጠባቢዋ አን ፍላኸርቲ "ከፍተኛ የወለድ መጠኖች የብድር አቅሞችን ይበልጥኑ እንዲቀንስ በማድርግ ዋጋዎች ዝቅ እንዲሉ ያደርጋል" ብለዋል።

እስካሁን በብሔራዊ ባንክ አማካይነት የተጣሉት ተከታታይ ስምንት የብድር ወለዶች የብድር አቅምን በ25 ፐርሰንት ዝቅ አድርገዋል።

የቤት ዋጋ መውረድ በተለያዩ የአውስትራሊያ ክፍለ አገራት ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖዎችን አሳድሯል?

ሜልበርን ውስጥ የቤት ዋጋ ከማርች 2020 ንፅፅሮሽ ጋር ሲስተያይ ከ1.5 ፐርሰንት በላይ ይገኛል።

አደላይድ፤ በተቃራኒው በ 1.5 ዝቅ ሲል፤ የቤት ዋጋው ከቅድመ ወረርሽኙ 42.8 ፐርሰንት በላይ ነው።

ሲድኒ፤ ከመላ አገሪቱ በፍጥነት ዋጋ የወረደበት ከተማ ሲሆን፤ ከጃኑዋሪ ከፍታው የ12 ፐርሰንት ቅንሳ አስመዝግቧል።
Change in Housing Price.png
Australia's property downturn has picked up the pace again, but Melbourne is the only capital city getting close to erasing the entirety of its pandemic upswing. Credit: CoreLogic Home Value Index 3 January 2023 / SBS News


Share
Published 5 January 2023 6:51pm
By Kassahun Seboqa Negewo, NACA
Source: SBS

Share this with family and friends