ከዛሬ ዲሴምበር 6 እኩለ ለሊት ጀምሮ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ቪክቶሪያ ላይ ተጥለው የነበሩ ገደቦች በተጨማሪ ረግበዋል።
- ከቤትዎ ሲወጡ ሁሌም የፊት ጭምብል ይዘው መውጣት ይጠበቅብዎታል
- በሕዝብ ትራንስፖርት፣ በታክሲ ወይም መኪና ተጋርተው ሲሔዱ ወይም የገበያ አዳራሾች፣ ሱቆችን በመሳሰሉ የመገበያያ ትላልቅ የችርቻሮ ሥፍራዎች ሲገኙ የፊት ጭምብል ማጥለቅ ግድ ይሰኛሉ
- በቤት ውስጥና ከቤት ውስጥ ውጪ ሆነው ከሌሎች ሰዎች የ1.5 ሜትር ርቀት ለመጠበቅ በማይችሉበት ሁኔታ ሲሆኑ የፊት ጭምብል እንዲያጠልቁ በብርቱ ይመከራል
- በቀን ቤትዎ ውስጥ እስከ 30 ያህል ጎብኚዎችን ተቀብለው ማስተናገድ ይችላሉ። ከቤትዎ ፊት ለፊትና ጓሮ ያሉ ሥፍራዎች እንደ ቤትዎ አካል ይቆጠራሉ።
- በውጪ የሕዝብ መገኛ ሥፍራዎች እስከ 100 ያህል ሰዎች በጋራ መሰባሰብ ይችላሉ።
- የንግድ ቤቶች የጎብኚዎቻቸውን ዝርዝር በኤሌክትሮኒክ ሬኮርድ መያዝ ይገባቸዋል።
- ምግብ ቤቶች፣ ካፌዎች፣ ቡና ቤቶችና መጠጥ ቤቶች ደንበኞቻቸውን ተቀምጠውም ሆነ የሚሹትን ይዘው ለሚሔዱ ግልጋሎቶቻቸውን መስጠት ይችላሉ። ደንበኞቻቸው የ1.5 ሜትር ርቅት መጠበቅ እንዲቻላቸው የሁለት ስኩየር ሜትር ደንብ ሊተገብሩ ይገባል።
- ሠርጎች፣ ቀብሮችና ቤተ እምነቶች ታዳሚዎቻቸውንን ያለ ገደብ ማስተናገድ ይችላሉ። የ1.5 ሜትር ርቅት መጠበቅ እንዲቻላቸው የሁለት ስኩየር ሜትር ደንብ ሊተገብሩ ይገባል። መስተንግዶዎቹ ወይም ግልጋሎቶቹ የሚከናወኑት በቤት ውስጥ ከሆነ የጎብኚዎች ቁጥር ከ30 መብለጥ የለበትም።
- በቡና ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች እንዲሁም ሠርጎች ላይ የዳንስ ወለሎች ዳግም ክፍት ሆነው ማስተናገድ ይችላሉ። የ1.5 ሜትር ርቅት መጠበቅ እንዲቻላቸው የሁለት ስኩየር ሜትር ደንብ ሊተገብሩ ይገባል። በአንድ የዳንስ ወለል ላይ ከ50 ሰዎች በላይ መደነስ አይፈቀድም።