ከዘንድሮው የፌዴራል በጀት ሥራ ፈላጊዎች፣ የመብራት ክፍያ ለመክፈል የኑሮ ትግል ላይ ላሉ፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤት ተከራዮች፣ የአረጋውያን ክብካቤ ሠራተኞች፣ አንስተኛ የንግድ ተቋማት፣ የታዳሽ ኃይል ሙዋዕለ ንዋይ አፍሳሽ አውስትራሊያውያን በቢሊየን የሚቆጠር የድጎማና ደመወዝ ጭማሪ ያገኛሉ።
በጅሮንድ ጂም ቻልመርስ አውስትራሊያ $4.2 ቢሊየን ዶላርስ ተረፈ ፈሰስ እንዳገኘችና ይህም በ15 ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያው መሆኑን ገልጠዋል።
የ2023 / 24 የበጀት ጉድለት ወደ $13.9 ቢሊየን ለመውረድ በቅቷል።
ከዘንድሮው የፌዴራል በጀት ተጠቃሚዎች
- ላጤ ወላጆች የመጨረሻ ልጃቸው ዕድሜ 14 ዓመት እስኪሞላ ድረስ ተጨማሪ ድጎማ ያገኛሉ
- ከአምስት ሚሊየን በላይ የሆኑ ሰዎች የ$500 ከአንድ ሚሊየን በላይ አነስተኛ ንግዶች $650 ድጎማዎችን በተናጠል ያገኛሉ
- የኃይል ምንጭ ለመቀነስ እስከ 111, 000 መኖሪያ ቤቶች ለሶላር ፓናል ወይም ድርብ አንፀባራቂ መስኮቶች ማስገጠሚያ የ$1.3 ቢሊየን ድጎማ ያገኛሉ
- የዋጋ ቅናሽ ካርድ ባለቤቶች፣ ልጆች ያላቸው ቤተሰቦችና ተጠዋሪዎች በአካልና በስልክ የጠቅላላ ሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ $3.5 ቢሊየን ተመድቦላቸዋል
- የሥራ ፈላጊዎች ክፍያ ከሴፕቴምበር 20 ቀን 2023 አንስቶ በአሥራ አራት ቀን የ$40 ጭማሪ ያገኛሉ
- የአረጋውያን ክብካቤ ሠራተኞች የ$141 ቢሊየን ጭማሪ ያገኛሉ
- የአነስተኛ ቤት ተከራዮች በ14 ቀናት ክፍያቸው ላይ እስከ $31 ተጨማሪ የኪራይ ድጎማ ያገኛሉ
- አርተፊሻል ኢንተለጀንስን ለመሰለ አዲስ የቴክኖሎጂ ዘርፍ $100 ሚሊየን ተመድቧል
- ለሥነ ጥበብና ባሕል $286 ሚሊየን ተመድቧል
- ለሕፃናት ክብካቤ ለአራት ዓመታት $55.3 ቢሊየን የተመደበ ሲሆን 1.2 ሚሊየን ቤተሰቦች ተጠቃሚዎች ይሆናሉ
- ለማሕበረሰብ ተኮር ድርጅቶች $200 ሚሊየን ተመድቧል
ዕዳ፣ ተረፈ ፈሰስና ደመወዝ
- የአውስትራሊያ የተጣራ ዕዳ 2022/23 $548.6 ቢሊየን
- 2023/24 $574.9 ቢሊየን
- ተረፈ ፈሰስ 2022/23 $4.2 ቢሊየን
- 2022/23 የደመወዝ ዕድገት 3.75%
- 2023/24 የደመዝ ዕድገት 4%
- 2024/25 የደመወዝ ዕድገት 3.25%
- 2025/26 የደመወዝ ዕድገት 3.25%
- 2026/27 የደመወዝ ዕድገት 3.5%