ሙሉቀን መለሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ሙለቀን መለሰ ሕይወቱ ያለፈው በሚኖርበት ሀገረ አሜሪካ ነው

Muluken Melese.png

Muluken Melese. Credit: Supplied

ከሶስት አስርት ዓመታት ባለይ በሀገረ አሜሪካ ኑሮውን ያደረገው ሙሉቀን መለሰ የሙዚቃውን ዓለም በመተው በመንፈሳዊ የሙዝሙር ስራዎች ውስጥ ያሳልፍ እንደነበር ይታወሳል።

ሙሉቀን መለሰ በጎጃም ክፍለ ሀገር አነደድ ወረዳ ውስጥ ዳማ ኪዳነ ምሕረት በምትባል መንደር በ1946 ዓ.ም እንደተወለደ ግለታሪኩ ያወሳል።

አሥር ዓመት ሲሆነው እናቱ ስለሞቱ፤ አዲስ አበባ ይኖሩ ከነበሩ አጐቱ ጋር እንዲማር ብለው ያመጡት ሙሉቀን መለሰ ኮልፌ ሰፈር ጳውሎስ ትምህርት ቤት ሊገባ ችሏል።

ለሙዚቃ ልዩ ፍቅር የነበረው ድምፃዊው እርሱ በነበረበት አከባቢ በተከፈተው የሙዚቃ ትምህርት ቤት ገብቶ በአቶ ተፈራ አቡነ ወልድ አማካይነት ለስድስት ወራት የዘለቀ የትምህርት እገዛ አግኝቷል።

ገና የ13 ዕድሜ ታዳጊ ሳለ ሙዚቃን የጀመረው ድምፃዊው በ1958ዓ.ም በፈጣን ኦርኬስትራ ውስጥ ተቀላቅሎ በመግባት ለሁለት ዓመታት ያህል መስራት ችሏል።


Share

Published

By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends