የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነሐሴ 3 ቀን 2016 ባወጣው መግለጫ ለሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የሰጠ መሆኑን አስታወቀ።
ቦርዱ ከሕጋዊ ሰውነት ማላበሻው ውሳኔ ላይ የደረሰውም ሕወሓት ሐምሌ 19 ቀን 2016 ያቀረበውን የሕጋዊ ሰውነት ጥያቄ ደብዳቤና የማሻሻያ ዐዋጁን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፍትሕ ሚኒስቴር ሕወሓት ሕገ መንግሥታዊና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓቱን አክብሮ ለመንቀሳቀስ መስማማቱን በመግለጡ በልዩ ሁኔታ እንዲመዘገብ ተደርጓል ሲል አመላክቷል።

Credit: NEBE
ሕወሓት በልዩ ሁኔታ የመመዝገብ ውሳኔን የያዘው የምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ከደረሰው ዕለት አንስቶ ባሉት ስድስት ወራት የቦርዱ ታዛቢዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባኤ በማድረግ መተዳደያ ደንቡን አስፀድቆ፤ አመራር አባላቱን የሚያስመርጥ ይሆናል።
ፓሪስ ኦሎምፒክ 2024
ከጁላይ 26 / ሐምሌ 19 አንስቶ ፍፃሜው እሑድ ነሐሴ 5 / ኦገስት 11 በሚሆነው የፓሪስ ኦሎምፒክ 2024 ተወዳዳሪ ከሆኑ 184 ሀገራት ውስጥ 80ዎቹ በተወዳደሩባቸው 32 የስፖርት ዘርፎች ድል በመንሳት ከወርቅ እስከ ነሐስ ያሉ ሜዳሎችን ለመሸለም በቅተዋል።
እስከ ፓሪስ ኦሎፒክ 2024 ፍፃሜ ዋዜማ ድረስ፤
- ዩናይትድ ስቴትስ፤ 33 ወርቅ 39 ብር 39 ነሐስ በድምሩ 111 ሜዳሎችን በማግኘት 1ኛ
- ቻይና፤ 33 ወርቅ 27 ብር 23 ነሐስ በድምሩ 83 ሜዳሎችን በማግኘት 2ኛ
- አውስትራሊያ፤ 18 ወርቅ 16 ብር 14 ነሐስ በድምሩ 48 ሜዳሎችን በማግኘት 3ኛ
- ኢትዮጵያ 2 የብር ሜዳሎችን በማግኘት 68ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።