ምንም እንኳ በዛሬው ዕለት ቪክቶሪያ አራት በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎችን ብታስመዘግብም፤ ሜልበርንና ሪጂናል ቪክቶሪያ ላይ ተጥለው ያሉ የኮረናቫይረስ ገደቦች በተያዘላቸው ዕቅድ ይነሳሉ።
የቪቶሪያ ተጠባባቂ ፕሪሚየር ጄም ሜሊኖ ገደቦቹ ከዛሬ ሐሙስ ጁን 10 ከምሽቱ 11:59pm ጀምሮ ግብር ላይ መዋላቸው እንደሚያበቃ አስታውቀዋል።
ይሁንና በትናንትናው ዕለት ገደቡ ሲነሳ ከቤት ውጪ የፊት ጭምብል ማጥለቅ ግድ እንደማይል ቢነገርም ከዛሬው የቫይረስ ክስተት ጋር ተያይዞ ነዋሪዎች ከቤት ውጪ የፊት ጭምብል ማጥለቅ አለባቸው በሚለው ማስተካከያ ተደርጎበታል።
በአሁኑ ወቅት ቪክቶሪያ ውስጥ 78 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተው ያሉ ሲሆን፤ በትናንትናው ዕለት 23,679 የቪክቶሪያ ነዋሪዎች የቫይረስ ምርመራ አካሂደዋል 20,784 ክትባት ተከትበዋል።