እሑድ ነሐሴ 5 / ኦገስት 11 በፓሪስ ኦሎምፒክ የፍፃሜ ዋዜማ በተካሔደ የሴቶች ማራቶን ትዕግስት አሰፋ 2 ሰዓት ከ22 ደቂቃ 58 ሰከንድ በመጨረስ የሁለተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቅቃለች።
ኔዘርላንድስን ወክላ የሮጠችው የኢትዮጵያ ተወላጇ ሲፋን ሐሰን 2 ሰዓት ከ22 ደቂቃ 55 ሰከንድ በሆነ ውጤት በማሸነፍ የወርቅ ሜዳል ባለቤት ሆናለች።
በእዚሁ በፓሪስ ኦሎምፒክ የ5000 እና 10 ሺህ ሜትሮች የወርቅ ሜዳል አሸናፊ በመሆን በልዩ የኦሎምፒክ ታሪክ የክብር ሥፍራ ይዛለች።
ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪ 2 ሰዓት ከ23 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ በሆነ ውጤት 3ኛ ሆና ለነሐስ ሜዳል በቅታለች።
ኢትዮጵያ ትዕግስት አሰፋን ጨምሮ በአራት የኦሎምፒክ ውድድሮች በሴት አትሌቶቿ 2 የወርቅ 1 የብር እና 1 የነሐስ ሜዳሎችን አግኝታለች።
- ፋጡማ ሮባ፤ በ1996 የአትላንታ ኦሎምፒክ ወርቅ
- ቲኪ ገላና፤ በ2012 የለንደን ኦሎምፒክ ወርቅ (የኦሎምፒክ ሬኮርድ በመስበር 2:23:07)
- ማሬ ዲባባ፤ በ2016 የሪዮ ዴ ጄኒሮ ኦሎምፒክ ነሐስ
- ትዕግስት አሰፋ፤ በ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ የብር ሜዳሎችን አግኝታለች።
በፓሪስ ኦሎምፒክ 16ኛ የውድድር ዕለት ድረስ በ32 የስፖርት ዘርፎች በተካሔዱ ውድድሮች ቻይናና ዩናይትድ ስቴትስ የሜዳል ሠንጠረዥ ላይ አንደኛና ሁለተኛ በመሆን እየተፈራረቁ ደረጃዎቻቸውን ይዘው አሉ፤
- ቻይና፤ 39 ወርቅ 27 ብር 24 ነሐስ በድምሩ 90 ሜዳሎችን በማግኘት 1ኛ
- ዩናይትድ ስቴትስ፤ 38 ወርቅ 42 ብር 42 ነሐስ በድምሩ 122 ሜዳሎችን በማግኘት 2ኛ
- አውስትራሊያ፤ 18 ወርቅ 18 ብር 14 ነሐስ በድምሩ 50 ሜዳሎችን በማግኘት 3ኛ
- ኢትዮጵያ 1 ወርቅ 3 ብር በድምሩ 4 ሜዳሎችን በማግኘት 45ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።