የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቅ ተቋም "ተጎጂዎች በክልል የፀጥታ አካላትና በመንግሥት ላይ እምነት ማጣታቸው በእጅጉ አሳስቦኛል" አለ

"ትምህርት ቤቶች (የትምህርት ተቋማት) ከማኛውም ዓይነት የሃይማኖት፣ የፖለቲካ አመለካከትና ባሕላዊ ተፅዕኖዎች ነፃ እንደሆኑ በሕግ በተደነገገበት ሁኔታ የአማራን/የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችን/የሲዳማን ወይም ወይም የሌላ ክልልን ባንዲራ በትምህርት ቤት ማውለብለብና ክልላዊ መዝሙር እንዲዘመር ማስገደድ የሕግም ሆነ የሞራል መሠረት አለው ብሎ ተቋማችን አያምንም" የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም

IDP camp.jpg

A woman listens as other IDP's recount their experiences of forced displacement from their homes in Wollega at the Children's Growing Center IDP camp on April 4, 2022 in Hayk, Ethiopia. Credit: J. Countess/Getty Images

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ታሕሳስ 3 ቀን 2015 ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በትምህርት ቤቶች የተከሰተውን ችግር በተመለከተ፣ የመንግሥት አገልግሎቶችን ከሙስናና ብልሹ አሠራር የፀዱ ለማድረግ የግልፀኝነትና ተጠያቂነት አሠራራ ሥርዓት መዘርጋት እንዳለበት የሚጠቁም እንዲሁም በወለጋ አካባቢ የደረሰውን የዜጎች ሞትና መፈናቀል አስመልክቶ ማሳሰቢያዎችን ሰጥቷል።

1. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በትምህርት ቤቶች የተከሰተውን ሁከትና ብጥብጥ በተመለከተ

  • "ትምህርት ቤቶች (የትምህርት ) ማኛውም ዓይነት የሃይማኖት፣ የፖለቲካ አመለካከትና ባሕላዊ ተፅዕኖዎች ነፃ እንደሆኑ በሕግ በተደነገገበት ሁኔታ የአማራን/የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችን/የሲዳማን ወይም ወይም የሌላ ክልልን ባንዲራ በትምህርት ቤት ማውለብለብና ክልላዊ መዝሙር እንዲዘመር ማስገደደ የሕግም ሆነ የሞራል መሠረት አለው ብሎ ተቋማችን አያምንም።
  • የሌላ ክልል ሰንደቅ ዓላማ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥ ይሰቀል የሚባልበት በቂ ምክንያት የሚኖር ከሆነም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን ፈቃድና ይሁንታ ማግኘት ይገባዋል።
  • በመሆኑም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የአንድን ክልል ሰንደቅ ዓላማ ለማውለብለብና የክልሉ መዝሙር በተማሪዎች እንዲዘመር በሚደረገው የማስገደድ ድርጊት ሳቢያ በተማሪዎች ላይና በሕዝብ ንብረት ለሚደርሰው ጥፋት ተጠያቂው የከተማ አስተዳደሩ እንጂ ሌላ ውጫዊ አካል በለመሆኑ ለችግሩ መንስኤ የሆኑት የከተማ አስተዳደሩ አስፈፃሚ አካላት ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል።
  • የኦሮሚያ ክልል ሊያገኛቸው የሚገቡ ልዩ ልዩ ጥቅሞችና የአፈፃፀም ሥርዓት በግልፅ በሕግ ባልተደነገገበት ሁኔታ በትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ ሰንደቅ ዓላማ በትምህርት ቤቶች እንዲሰቀልና ሁሌም ሰንደቅ ዓላማ የመስቀል ሥነ ሥርዓት ሲፈፀም የኦሮሚያ ክልል መዝሙርን እንዲዘምሩ የማስገደድ ድርጊት በግለሰብ የመንግሥት ባለስልጣኖች እየተፈፀመ ያለ ቢሆንም ድርጊቱ የፌዴራል ሥርዓቱን መሠረታዊ መርህ የሚጥስ ከመሆኑም በተጨማሪ በሕዝቦች መካከል ፀንቶ የኖረው የአንድነትና የእኩልነት መስተጋብር ዕሴትን የሚበጣጥስ በዚህም ለመልካም አስተዳደር እጦት መንሴ በመሆኑ በከተማ አስተዳደሩ በኩል ተገቢው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።
    Adanech Abebe .jpg
    Adanech Abiebie, Mayor of Addis Ababa. Credit: Minasse Wondimu Hailu/Anadolu Agency via Getty Images
    2. የመንግሥት እልግሎቶችን ከሙስና ለመከላከል የግልፀኝነት አሠራር መጠናከር
  • ሃብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ግዴታ የተጣለባቸው (ተሿሚ፣ ተመራጭ ወይም የመንግሥት ሠራተኛ) በከፍተኛ የስልጣን ረጃ ላይ የሚገኙና በግለሰብና በቡድን ጥቅም ላይ አሉታዊ ሚና ያለው ውሳኔ የሚያስተላልፉ በመሆኑ በዚያው ልክ ላልተገባ ጥቅምና ለሕገ ወጥ ሃብት ስብሰባ በቀላሉ የተጋለጡ ስለሆነ የእነዚህ ግለሰቦች አስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥና አሠራር እንዲሁም የግለ ሃብትና ንብረት ከሕዝብ ዓይንና ጆሮ ሊደበቅ አይገባም።... በመሆኑም የሃብት ምዝገባው መረጃ ለሕዝብ ክፍት እንዲሆን የእርምት እርምጃ እንዲወሰድበት ምክረ ሃሳብ አቅርበናል።
    EIO.jpg
    Credit: EIO

    3. የሕግ የበላይነትን ማስከበርና የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅ መንግሥታዊ ግዴታ
  • መንግሥት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገራችን አንዳንድ አካባቢዎች እይተስተዋለ ያለውን የተደራጀ ወንጀል ማለትም የደቦ ፍርድ፣ ማንነትና የፖለቲክ አመለካከትን መሠረት ያደረገ ጥቃትና ጅምላ ማፈናቀል እንዲሁም ሕዝቡን እራሱን፣ ቤተሰቡንና ንብረቱን ከመሰል ጥቃት እንዲከላከልና እንዲጠብቅ አስቀድሞ መረጃ መስጠት እንዳለብት ተቋማችን በተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ቢያቀርብም ችግሩ እየሰፋና የድርጊቱ አፈፃፀምም እየረቀቀ መምጣቱ፤ በዚህም ተጎጂዎች በክልል የፀጥታ አካላትና በመንግሥት እምነት ማጣታቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን በጅጉ አሳስቦታል።
  • ለዚህም በምሥራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን ሸዋና ምሥራቅ ሽዋ ዞኖች በመንግሥት አእሸባሪ ተብሎ በተፈረጀውና ዘኔ በሚባለው የታጠቀ ቡድን ተፈፀመ እየተባለ በተጎጂዎች በስፋት የሚነገረው ግድያና ጅምላ ማፈናቀል ድርጊት በቂ ማሳያ ነው።
  • በእነዚህ አካባባኢዎች ስለተፈፀመው ሕገ ወጥ ድርጊት፣ ድርጊቱን በፈፀሙት አካላት ላይ ስለተወሰደው ሕጋዊ እርምጃና ተፈናቃዮችን ወደ ነበሩበት ሁኔታ ለመመለስ ስለተወሰደው አስተዳደራዊ ውሳኤን አስመልክቶ የክልሉም ይሁን የፌዴራል መንግሥት ዝምታ ተቋሙን ይበልጥ አሳስቦታል።

    የዕንባ ጠባቂ ተቋሙ መግለጫውን ሲያጠቃልልም "መንግሥት ስልጣንና ተግባሩን በሕገ መንግሥቱ መርሆዎች መሠረት የመሥራት ግዴታ አለበት" ሲል አመላክቶ "የአንድ ሕዝብ የአደረጃጀት ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ምላሽ ካገኘ የሌላው ሕዝብ አደረጃጀት ጥያቄ ምላሽ የማያገኝበት ምክንያት አይኖርም" ብሏል።

Share

Published

By Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends