ኢራን እሥራኤል ላይ የድሮንና ሚሳይል ቀጥተኛ ጥቃት ሰነዘረች

እሥራኤል የመከላከልም ሆነ የማጥቃት ከፍተኛ ብቃት ወይም ስንዱነት አለኝ ብላለች

Iran Israel.jpg

Israel says its military is ready to deal with drone and missile strikes by Iran. Credit: Abir Sultan

ኢራን ዛሬ እሑድ ማለዳ ላይ በደርዘኖች የሚቆጠሩ ድሮኖችና ቦለስቲክ ሚሳይሎችን እሥራኤል ላይ ወንጭፋለች።

ኢራን እሥራኤል ላይ ጥቃት ለመሰንዘር አስባብ ያደረገችው እሥራኤል ሶሪያ በሚገኘው የኢራን ቆንሱላ ጽሕፈት ቤቴ ላይ ባደረሰችው የአየር ጥቃት የሁለት ጄኒራሎቼን ሕይወር አጥፍታለች በሚል ነው።

ይሁንና እስካሁን ድረስ እሥራኤል በሶሪያ የኢራን ቆንሱላ ጽሕፈት ቤት ላይ ጥቃት ስለማድረሷ የማረጋገጫም ሆነ የማስተባበያ ቃል አልሰጠችም።

ከ1979ኙ የስላማዊ አብዮት ወዲህ ኢራን በእሥራኤል የቀጥታ ጥቃት ስትፈጽም ይህ የመጀመሪያዋ ነው።  

የእሥራኤል ወታደራዊ ቃል አቀባይ ሪር አድሚራል ዳንኤል ሃጋሪ በበኩላቸው፤ የኢራን ጥቃት አደገኛ የግጭት ማባባስ እርምጃ እንደሆነ ጠቅሰው፤ እሥራኤል የመከለከልም ሆነ የማጥቃት ከፍተኛ ብቃት ወይም ስንዱነት ያላት መሆኑን ገልጠዋል።  

ጥቃቱን ተከትሎ የደረሱ ጉዳቶች በዝርዝር አልተመለከቱም።

በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁና የተመራው የእሥራኤል ካቢኔና በፕሬዚደንት ጆ ባይደን የተመራው ካቢኔ የኢራንን ጥቃት አስመልክተው መክረዋል።

እሥራኤል የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤትም እንዲመክርበት ጥሪ አቅርባለች።

አውስትራሊያ የኢራንን ጥቃት አውግዛለች።


 



 


 

Share

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo, NACA
Source: SBS

Share this with family and friends