ኢትዮጵያ አማርኛ የአፍሪካ ሕብረት የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ጠየቀች

44ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው። የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች የሚሳተፉበት ይህ የሕብረቱ ሚንስትሮች ስብሰባ ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል።

African Union .jpg

Credit: LUDOVIC MARIN/AFP via Getty Images / Jerry Holt/Star Tribune via Getty Images

በዚህ ጉባዔ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አፍሪካ ሕብረት የአማርኛ ቋንቋን የሥራ ቋንቋው እንዲያደርግ ጥያቄ አቅርበዋል።


 ሚንስትሩ በንግግራቸው አክለውም "የቀድሞው አፍሪካ አንድነት ድርጅት አማርኛ አንደኛው የሥራ ቋንቋ እንደሚያደርግ በወቅቱ ተነግሮ ነበር፣ ይህ እስካሁን ውሳኔ ሳያገኝ ቆይቷል" ብለዋል።



አፍሪካ ሕብረት ከአንድ ዓመት በፊት በምስራቅ አፍሪካ በስፋት የሚነገረው ስዋህሊ ቋንቋን የህብረቱ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ወስኖ ነበር።


የአፍሪካ ሕብረት አሁን ላይ ስዋህሊን ጨምሮ እንግሊዝኛ ፣ፈረንሳይኛ፣ አረብኛ፣ ስፓኒሽ እና ፖርቹጊዝ የስራ ቋንቋው አድርጓል።



የሕብረቱ የሚንስትሮቹ ስብሰባ የፊታችን ቅዳሜ እና እሑድ በሚካሄደው የሕብረቱ መሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ አንኳር አጀንዳዎች ላይ በመወያየት የውሳኔ ሀሳቦችን ማዘጋጀት ላይ ያተኩራል ተብሏል።


ዘንድሮው የሕብረቱ መሪዎች ጉባኤ ዋነኛ ትኩረቱን በትምህርት ልማት ላይ እንደሚያደርግ ተገልጿል።




Share

Published

By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends