የዩናይትድ ስቴትስ - አፍሪካ መሪዎች መድረክ በመጀመሪያው የመክፈቻ ቀኑ የአፍሪካና ወጣት የዲያስፖራ መሪዎችንና ሌሎች ባለድርሻዎችን አካትቶ በተለያዩ ርዕሰ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቷል።
ሁለተኛ ቀኑን በንግድና ሙዋዕለ ንዋይ ፍሰት ላይ አተኩሮ አገባድዷል።
በመጀመሪያው ዕለት ታህሳስ 4 በተካሔደው መድረክ የመወያያ አጀንዳዎቹ የነበሩት የንግድና ሙዋዕለ ንዋይ ፍሰት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ሰላም፣ ደኅነት፣ አስተዳደርና የሕዋ ትብብር ነበሩ።
በቀጣዩ ዕለትም ከ300 በላይ የአሜሪካና የአፍሪካ ኩባንያዎች ከፍተኛ ተወካዮች በተገኙበት የተካሔደ ሲሆን፤ ትኩረቱም የሁለትዮሽ ንግድና ሙዋዕለ ንዋይ ፍሰት፣ ጤና፣ መሠረተ ልማት፣ የኃይል ምንጭ፣ የእርሻ ንግድና ዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ ነበር።

U.S. President Joe Biden delivers remarks at the U.S. - Africa Leaders Summit on December 14, 2022 in Washington, DC. The Summit brings together heads of state, government officials, business leaders, and civil society to strengthen ties between the U.S. and Africa. Credit: Kevin Dietsch/Getty Images
ፕሬዚደንቱ የዩናይትድ ስቴትስ - አፍሪካ ንግድ መድረክን አካትቶ የዩናይትድ ስቴትስ - አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሬዚደንት ኦባማ አማካይነት በ2014 ሲጀመር እሳቸው ምክትል ፕሬዚደንት ሆነው ጅማሮን "ለጋራ ዘላቂ ስኬት" እንዲበቃ አስተዋፅዖ ማድረጋቸውን አውስተዋል።
አክለውም፤ አፍሪካ በርካታ ተግዳሮች እይፈተኗት ያለች አኅጉር መሆኗን አመላክተው "እነዚህን ሁሉ ሁሉንም ተግዳሮቶች ያለ አፍሪካውያን አመራር ልንፈታው አንችልም" ሲሉ ለተግዳሮቶቹ መክሊያ የሚሆኑ የመፍትሔ ዕሳቤዎችና ፈጠራዎች በእያንዳንዱ እርምጃ የአፍሪካን ሕዝብ አስተዋፅዖ አካትቶ የጋራ አመራር ትብብሩን የሁለትዮሽ ፋይዳ ልብ አሰኝተዋል።
አቶ ባይደን አስተዳደራቸው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ለአፍሪካ 231 ሚሊየን ክትባቶችን ለ49 የአፍሪካ አገራት መላኩን፣ አፍሪካ የእራሷን ክትባቶች ለማምረትና ለማቅረብ እንድትበቃም ሙዋዕለ ንዋይ ማፍሰሱንና የምግብ ዋስትና ፕሮግራምንም ማጠናከሩን አመላክተዋል።

Attendees of the US - Africa Leaders Summit walk through the Walter E. Washington Convention Center, the site of the summit that brings together leaders from across Africa to meet with US President Joe Biden and other US representatives, in Washington, DC, December 13, 2022. Credit: SAUL LOEB/AFP via Getty Images
አያይዘውም፤
- አፍሪካንና ዩናይትድ ስቴትስን ይበልጥኑ በማስተሳሰር አዳዲስ ዕድሎችን ለመፍጠር አገራቸው ከአፍሪካ አኅጉር የነፃ ገበያ አካባቢ ሴክሬታሪያት ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ታሪካዊ የሆነ የመግቢያያ ሰነድ መፈራረሟን፣
- መሠረተ ልማትን አካትቶ አፍሪካ ውስጥ ቀጣናዊ ንግድን ለማሳለጥ የሙዋዕለ ንዋይ ፍሰት መቀጠልን፣
- ፈጠራና ሥራ ፈጣሪነትን ለማጎልበት አፍሪካና ሕዝቧ ላይ ሙዋዕለ ንዋያችንን ማሰሱን እንቀጥልበታለን ብለዋል።
አፍሪካን በዲጂታል ምጣኒ ሃብት ተሳታፊ ለማድረግ እንዲያግዝ ከግማሽ ቢሊየን ዶላር በላይ ለማዋል ከኮንግረስ ጋር መምከራቸውን ተናግረዋል። ይህም ማለት ከማይክሮሶፍትና ቫያሳት ጋር በመተባበር 5 ሚሊየን አፍሪካውያን የኢንተርኔት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻልና በ2025 መጨረሻም 100 ሚሊየን አፍሪካውያን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻልን ያካተተ መሆኑን አመላክተዋል።
ፕሬዚደንት ባይደን ንግግራቸውን ከማስደመጣቸው በፊት የሞሮኮንና የአርጀንቲናን የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ግጥሚያ ተመልክተዋል።
ከፕሬዚደንት ባይደን ቀደም ብለው ለንግድ ማኅበረሰቡ ንግግር ያደረጉት የዩናይትድ ስቴት ስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በበኩላቸው፤
"የጭ ግብ አትና አቅርቦት የጋራ ድርሻዎቻችንን በ አ ፐሰንት ከፍ ማድረግ ከቻልን ተጨማሪ 35 ቢሊየን ዶላርስ ለአፍሪካ 25 ቢሊየን ዶላርስ ገቢ ለዩናይትድ ስቴትስ ማስገባትና ከ250,000 በላይ ባለ ጥሩ ክፍያ ስራዎችን መፍጠር እንችላለን" ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በተጨማሪም ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር የጎንዮሽ ውይይት ያካሔዱ ሲሆን፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋርም ተገናኝተው በቅርቡ በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥትና ሕወሓት መካከል የተካሔዱትን የፕሪቶሪያና ናይሮቢ የሰላም ስምምነቶች አንስተው ተነጋግረዋል።
የመሪዎቹ ዋነኛ የውይይት መድረክ ዛሬ ተካሒዶ የሚጠናቀቅ ይሆናል።
በመርሃ ግብሩም መሠረት፤
- መልካም አስተዳደር፣ ዲሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብቶች ከበሬታና የሕግ የበላይነት
- ሰላማዊና ደኅንነቷ የተጠበቀ አፍሪካ
- አካታች ዕድገትንና ዘላቂ ልማትን መሠረቷ ያደረገች የበለፀገች አፍሪካ
- ሉላዊ ተግዳሮቶችን ከአፍሪካ ጋር ለመግጠም ሕብረብሔራዊ ሽርካዎች
- የመሪዎች ቤተሰባዊ ፎቶ ሥነ ሥርዓት
- የምግብ ዋስትናን ማስተዋወቅና የሥርዓተ ምግብ ተገዳዳሪነት ፕሮግራሞች ይከናወናሉ።