የፋይዘር ኮሮናቫይረስ ክትባት ዕድሜያቸው ከ60 በታች ላለ እንዲሰጥ ተባለ

*** ዕድሜያቸው ከ60 በላይ የሆኑቱ የአስትራዜኔካ ኮሮናቫይረስ ክትባትን በመከተቡ ይቀጥላሉ

AstraZeneca vaccine

Nurse Emeldah Mufara administers the AstraZeneca vaccine to Margaret Donnellan at the Sydney West COVID Vaccine Centre on May 07, 2021 in Sydney, Australia. Source: Getty

የአውስትራሊያ ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን ባቀረበው ምክረ ሃሳብ መሠረት ዕድሜያቸው ከ60 በታች የሆኑ የፋይዘር ኮሮናቫይረስ ክትባት እንዲከተቡ ተወሰነ።

የአማካሪ ቡድኑ ከዚህ የምክረ ሃሳብ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ ግድ የተሰኘው ከአስትራዜኔካ የኮሮናቫይረስ ክትባት ተያያዥነት ባለው የደም መርጋት ሳቢያ ሁለት ግለሰቦች ሕይወታቸውን በማጣታቸው ነው።

ባለፈው ሳምንት አንዲት የ52 ዓመት የኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪ፤ በኤፕሪል ወር ውስጥም እንዲሁ አንዲት የ48 ዓመት የኒው ሳዝ ዌይልስ ነዋሪ ሕይወታቸውን አጥተዋል።  

ቀደም ሲል ዕድሜያቸው ከ60 በታች ሆኖ የመጀመሪያ ዙር የአስትራዜኔካ ክትባትን የተከተቡና በጤናቸው ላይ ዕውክታን ያላሳደረባቸው ግለሰቦች የሁለተኛውን ዙር ክትባታቸውንም ተመሳሳዩን ክትባት እንዲወስዱ ተመክሯል።

የፌዴራል መንግሥቱ ይህንኑ ምክረ ሃሳብ የተቀበለ መሆኑንና ዕድሚያቸው ከ40 እስከ 59 ላሉት ሰዎች የፋይዘር ክትባትን እንዲከተቡ እንደሚያደርግ የጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት ተናግረዋል።  

ይሁንና የአውስትራሊያ ፋይዘር ክትባት አቅርቦት ውስን በመሆኑ የክትባት ዕድሜ ለውጡ የክትባት ሂደቱን ይበልጡኑ እንደሚያጓትተው ይጠበቃል።    

 

 

 


Share
Published 17 June 2021 2:31pm
By NACA
Presented by Kassahun Seboqa Negewo

Share this with family and friends