የቀድሞው የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬቨን ራድ በዩናይትድ ስቴትስ የአውስትራሊያ አምባሳደር ሆነው ተመደቡ

ዶ/ር ኬቨን ራድ አዲሱ ምደባቸውን አስመልክተውም ታላቅ ክብር እንደሚሰማቸውና ባለፈው አሠርት ዓመት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከዲሞክራትና ሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት፣ የንግድ ሰዎች፣ ሲቪል ሕብረተሰብና ሚዲያ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት መመሥረታቸውን ለሥራቸው መቃናት ጠቃሚ አስተዋፅዖ እንድሚኖረው አመላክተዋል።

The former PM of Australia, Kevin Rudd.jpg

The former Prime Minister of Australia, Kevin Rudd. Credit: Michael Gottschalk/Photothek via Getty Images

የአውስትራሊያ 26ኛው ቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር (2007 - 2010 / ጁን 2013 - ሴፕቴምበር 2013) ኬቨን ራድ በዩናይትድ ስቴትስ 23ኛው የአውስትራሊያ አምባሳደር ሆነው በተቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ ተመድበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አልባኒዚ "አቻ የለሽ ልምድ" ያካበቱት አቶ ራድ በዩናይትድ ስቴትስ የአውስትራሊያ አምባሳደር ሆኖ መመደብ በዩናይትድ ስቴትስ ዓይን የሚታየው "በጣሙን ሁነኛ ምደባ" ተደርጎ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

ኬቨን ራድ ቀደም ሲል፤
  • ከ 27 ጁን 2013 – 18 ሴፕቴምበር 2013 ጠቅላይ ሚኒስትር
  • ከ 3 ዲሴምበር 2007 – 24 ጁን 2010 ጠቅላይ ሚኒስትር
  • ከ 14 ሴፕቴምበር 2010 – 22 ፌብሪዋሪ 2012 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
  • ከ 4 ዲሴምበር 2006 – 3 ዲሴምበር 2007 የአውስትራሊያ ሌበር ፓርቲና የፌዴራል ተቃዋሚ ቡድን መሪ ሆነው አገልግለዋል።
ኬቨን ራድ ከአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ በቻይና ጥናቶች በክብር ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን፤ የማንደሪን ቋንቋን አጥርተው የሚናገሩና በቻይና ፖለቲካዊና ስትራቴጂያዊ ትንታኔ ተጠባቢነት በዩናይትድ ስቴትስ ዩኒቨርሲቲዎችና ሚዲያ ዘንድ ተቀባይነትን ማሳደር ችለዋል።

በ2022 የቻይናውን ፕሬዚደት ሺ ጂፒኒንግ ዓለም አቀፍ ዕይታና የቻይናና ዩናይትድ ስቴትስ መካከል አውዳሚ ግጭቶችን ለማስወገድ ብልሃትን የሚያመላክት "እጅግ ጥልቅ ጥናታዊ ትንታኔ" ተብሎ የወደሰለትን የመመረቂያ ፅሑፋቸውን አቅርበው ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

አቶ ራድ የእስያ ሕብረተሰብ ተቋም ዋና ሥራ አስፈፃሚና ፕሬዚደንት በመሆን ከ2021 ጀምሮ እየሠሩ ይገኛሉ።

አዲሱ ምደባቸውን አስመልክተውም ታላቅ ክብር እንደሚሰማቸውና ባለፈው አሠርት ዓመት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከዲሞክራትና ሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት፣ የንግድ ሰዎች፣ ሲቪል ሕብረተሰብና ሚዲያ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት መመሥረታቸውን ለሥራቸው መቃናት ጠቃሚ አስተዋፅዖ እንድሚኖረው አመላክተዋል።
በተያያዥነትም የአውስትራሊያ ኢንዱስትሪ ቡድን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሂዘር ሪድአውት በኒው ዮርክ የአውስትራሊያ ቆንሱላ ሆነው ተመድበዋል።
Heather Ridout, chief executive officer of the Australian Industry Group.jpg
Heather Ridout, chief executive officer of the Australian Industry Group. Credit: Ian Waldie/Bloomberg via Getty Images
በታካይነትም ለዚምባቡዌ፣ ትሪኒዳድ እና ቶቤጎ፣ እሥራኤል፣ ክሮኤሽያ፣ ኩክ ደሴቶችና ብራዚል አምባሳደሮች መሾማቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔኒ ዎንግ አስታውቀዋል።

Share

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends