የአውስትራሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔኒ ዎንግ ለአውስትራሊያ - ቻይና ታሪካዊ ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ቢጂንግ ገቡ

ቻይና የአውስትራሊያን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባለፉት አራት ዓመታት ጊዜያት ውስጥ ወደ ቤጂንግ ለዲፕሎማሲያዊ ንግግር ስትጋብዝ ይህ የመጀመሪያ ሲሆን፤ የአውስትራሊያና ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተመሠረተበት 50ኛ ዓመት ጋርም የተገጣጠመ ነው።

FM Penny Wong.jpg

Australian Foreign Affairs Minister Penny Wong arrives in Beijing, China, Tuesday, December 20, 2022. Credit: AAP Image/Lukas Coch

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዎንግ ቻይና የገቡት በቤጂንግ ሰዓት አቆጣጠር ማክሰኞ 10.38pm በአውስትራሊያ ሰዓት አቆጣጠር ረቡዕ 1.38am AEDT ነው።

ሚኒስትር ዎንግ ቤጂንግ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ በቻይና የአውስትራሊያ አምባሳደር ግራሃም ፍሌቸር አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ከቻይናው አቻቸው ዋንግ ዪ ጋር ተገናኝተው ሲነጋገሩ፤ ቻይና በዓመት ከ200 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ በሚያስገኙ በተለያዩ የአውስትራሊያ ምርቶች ላይ የጣለችቻቸው ማዕቀቦች ዋነኛ የመነጋገሪያ አጀንዳ እንደሚሆን ይጠበቃል።

በታካይነትም አውስትራሊያዊቷን ጋዜጠኛ ቼንግ ሊይን ጨምሮ ቻይና ውስጥ በእሥር ላይ የሚገኙ አውስትራሊያውያን ጉዳይም እንደሚነሳ ይታመናል።

ሴናተር ዎንግ ቻይና እንደገቡ ከቤጂንግ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከረጅም ዓመታት በኋላ ቻይና መገኘታቸው ማለፊያ እንደሆነ ጠቅሰው" የሁለቱን አገራት 50ኛ ዓመት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማክበር እንዲያስችል እዚህ በመገኘቴ ለቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ዕውቅናና ምስጋናዬን አቀርባለሁ" ብለዋል።

አያይዘውም፤ የጉብኝታቸው አንዱ ስኬት ንግግሩ እራሱ መሆኑን ልብ አሰኝተው፤ በርካታ ዕልባት ሊበጅላቸው የሚሹ ጉዳዮም እንዳሉ አመላክተዋል።



Share

Published

By Kassahun Seboqa Negewo, NACA
Source: SBS

Share this with family and friends