የሉናር የጥንቸል (ድመት) አዲስ ዓመት በአኅጉረ እስያ ዛሬ መከበር ጀመረ

የቪክቶሪያ መንግሥት በሜልበርን የአውስትራሊያ ቀን ክብረ በዓል ሰልፍ እንዳይካሔድ ወሰነ

Chinese Welcome Spring Festival.jpg

Children from a Yue Opera troupe wearing traditional costumes perform in the street to greet the Chinese New Year, the Year of the Rabbit, on January 18, 2023, in Nanjing, Jiangsu Province of China. Credit: Yang Bo/China News Service/VCG via Getty Images)

ለ 15 ቀናት የሚዘልቀው የሉናር አዲስ ዓመት ዛሬ ጃኑዋሪ 22 ጥር 14 በእስያ መከበር ጀምሯል።

የ2023 አዲስ ዓመት የጥንቸል (የድመት) ዓመት ነው።

በዘንድሮው የሉናር አዲስ ዓመት በምሥራቅ እስያ ከወረርሽኝ ገደብ መነሳት በኋላ ቤተሰቦች ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኝተው በጋር በመሰባሰብ የሚያከብሩት ዓመት ይሆናል።

በቻይና ትራንስፖርት ሚኒስቴር ግምት ከጃኑዋሪ 7 እስከ ፌብሪዋሪ 15 ባሉት ቀናት ውስጥ 2.1 ቢሊየን የአገር ውስጥ መንገደኞች እንደሚጓጓዙ ጠቁሟል።

የቻይናውያን የአዲስ ዓመት ጉዞ የዓለም ታላቁ 'የሰብዓዊ ፍጡር ፍልሰት' በሚል ይታወቃል።

 የሉናር አዲስ ዓመት ዞዲያክ ቀመር በአይጥ፣ ነብር፣ ድራጎን፣ እባብ፣ ፈረስ፣ ፍየል፣ ዝንጀሮ፣ አውራ ዶሮ፣ ውሻ እና አሳማ የተሰየመ የ12 ዓመታት ኡደት አለው።

የዘንድሮው ዓመት የድመት ዓመትን ከምታከብረው ቬይትናም በስተቀር አብዛኛው የእስያ አገራት የሚከብሩት የጥንቸል ዓመትን ነው።

ጥንቸል የዞዲያክ አራተኛዋ እንሰሳ ስትሆን፤ተምሳሌነቷም ረጅም ዕድሜ፣ አዎንታዊነት፣ ግንዛቤ፣ ጥንቃቄ፣ ብልህነት፣ አስተውሎትና ራስን መጠበቅ ናቸው።

የአውስትራሊያ ቀን ክብረ በዓል

የቪክቶሪያ ነባር ዜጎች ጉባኤ በሜልበርን ከተማ ይካሔድ የነበረውን የአውስትራሊያ ቀን ክብረ በዓል ሰልፍ በቪክቶሪያ መንግሥት የመሰረዝ ውሳኔ በመልካም ጎኑ እንደሚቀበለው አስታወቀ።

የቪክቶሪያ መንግሥት በአውስትራሊያ ቀን ክብረ በዓል ሰልፍ ፈንታ "ምልሰታዊ ዕይታ፣ ከበሬታና ክብረ በዓል" በሚል ኩነት ጃኑዋሪ 26 ለነባር ዜጎች የሐዘን ቀን መሆንን ለማስገንዘብ በፌዴሬሽን አደባባይ ተዘክሮ እንዲውል ያደርጋል።

ይህንኑ የመንግሥት ውሳኔ የተቃዋሚ ቡድን መሪ ጆን ፔሶቶ ለቤተሰብ ኩነት ሆኖ ይውል የነበረውን የአውስትራሊያ ቀን የሚያጨናግፍ እንደሆነና ፕሪሚየሩም ለውሳኔያቸው በቂ ማብራሪያ እንዲሰጡበት ጠይቀዋል።

ይሁንና የነባር ዜጎች ጉባኤ ተባባሪ ሊቀመንበር ማርከስ ስቲዋርት በበኩላቸው ውሳኔው ትርጉም ያለው ነው በማለት ድጋፋቸውን ቸረዋል።  











 


Share
Published 22 January 2023 2:23pm
Updated 22 January 2023 2:28pm
By Kassahun Seboqa Negewo, NACA
Source: SBS

Share this with family and friends