ዶዳይ ፋብሪካ የሚገነባቸው የባትሪ መለዋወጫ ጣቢያዎች የሞተር ባለቤቶች ሙሌት ተደርጎ የተጠቀሙት ባትሪን ለኩባንያው ሰጥተው ሙሌት የተደረገ ባትሪ የሚወስዱባቸው ጣቢያዎች መሆናቸው ተነግሯል፡፡
በኤሌክትሪክ የሚሠሩ የሞተር ብስክሌቶችን እና የባትሪ መለዋወጫ ጣቢያዎች በኢትዮጵያ ማምረት መጀመሩን የተናገረው የጃፓኑ ዶዳይ ኩባንያ ይህንኑ ለማቀላጠፍ የመንግሥት የልማት ድርጀቶች የበላይ ከሆነው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና ዶዳይ ማኑፋክቸርንግ በተፈራረመት የመግባቢያ ስምምነት መሰረት በመጪ አንድ ዓመት ውስጥ 100 የባትሪ መለዋወጫ ጣቢያ የሚገነባ ይሆናል፡፡
ወደፊት የመግባቢያ ስምምነቱ ዝርዝር ይፋ እንደሚሆንም ተገልጧል።
የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክሎችን የሚያመርተው ዶዳይ ኩባንያ ፉብሪካውን በአዲስ አበባ ጎተራ የተከለ ሲሆን ለዚህም 7 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት ማድረጉን አስታውቋል፡፡