የሕወሓትን ከአሸባሪ ድርጅነትነት ፍረጃ ባሕር መዝገብ መፋቅን ተከትሎ የቀድሞው የክልሉ ፕሬዚደንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አማካሪና የድርጅቱ ቃል አቀባይ የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾመዋል።
አቶ ጌታቸው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ሆነው መሾማቸው የተገለጠው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት መጋቢት 14 ቀን 2015 "የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ስለማቋቋም" በሚል ባወጣው ይፋ መግለጫ ነው።
ተጨማሪ ያንብቡ

ሕወሓት ከአሸባሪነት ተሰረዘ
ጽሕፈት ቤቱ የኢፌዴሪ ምክር ቤት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ባሳለፈው ውሳኔ መሠረትና በፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪካ የተካሔደውን የሰላም ስምምነት ተመርኩዞ የሚኒስትሮች ምክር ቤት መጋቢት 9 ቀን 2015 "የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር ደንብ" ማፅደቁንም አውስቷል።
አክሎም "ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎችን ውክልና የሚያረጋግጥና አካታች የሆነ አስተዳደር በማዋቀር የክልሉን አስፈፃሚ አካል የመምራትና የማስተባበር ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል" ብሏል።