በወርኃ ሜይ በሚካሔደው አገር አቀፍ ምርጫ የሌበር ፓርቲ ለድል በቅቶ መንግሥት ካቆመ መላ የአውስትራሊያ ሠራተኞች የግብር ቅናሽ እንደሚያገኙ በጅሮንድ ጂም ቻልመርስ ዛሬ ማክሰኞ ምሽት ለፓርላማ ባቀረቡት የ2025 - 26 በጀት እስከ 268 ዶላር እንዲሁም በቀጣዩ ዓመት እስከ 536 ዶላር የሚያገኙ መሆኑን ይፋ አድርገዋል።
አያይዘውም፤ የአውስትራሊያ በጀት በሚቀጥለው የፋይናንስ ዓመት የ42 ቢሊየን ዶላር ተረፈ ፈሰስ ጉድለት እንደሚያገኘው አስታውቀዋል።
ለተረፈ ፈሰሱ ጉድለት አስባብ ከሆኑት ውስጥ ሉላዊ የንግድ መስተጓጓል፣ የአየር ንብረት ለውጥ ያደረሰቻው ጉዳቶች ፣ የዩክሬይንና መካከለኛው ምሥራቅ ያስከተሏቸው መዘዞችን ነቅሰው ጠቅሰዋል።
የግብር ቅናሽን በተመለከተ ከጁላይ 1 ቀን 2026 የዓመት ገቢያቸው $18,201 ለሆነ 16 ፐርሰንት ገቢያቸው $45,000 ለሆነ ሠራተኞች 15 ፐርሰንት፤ ከዓመት በኋላ በተጨማሪ የ14 ፐርሰንት የግብር ቅናሽ ያገኛሉ።

Tax cuts for all workers have been announced in the 2025 federal budget. Credit: SBS News