በቀድሞው የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ታየ ደንደአ ላይ ክስ ተመሰረተ

የፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በአቶ ታየ ላይ "የጦር መሥሪያ አዋጅን በመተላለፍና ፀረ-ሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችን በማስተላለፍ" ክሶችን መሥርቷል

Taye Dendea.jpg

Former state minister for peace, Taye Dendea. Credit: ENA

የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደኣ ሚያዚያ 17 ቀን 2016
በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የቀረቡ ሲሆን፤ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 251/ሐ እና አንቀጽ 257/ሰ ስር የተመላከተውን ድንጋጌ እና የጦር መሳሪያ አዋጅን መተላለፍ እና "ፀረ ሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችን በማስተላለፍ በስማቸው በተከፈተ ማኅበራዊ ትስስር ገፅ ላይ ድጋፍ የሚገልጹ መልዕክቶችን በማስተላለፍ" የሚሉ ክሶች ተመስርቶባቸዋል።


አቶ ታየ ከሚኒስትር ደኤታ የሥራ ኃላፊነታቸው የተነሱት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሲሆን በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉት ታህሳስ 2 ነው።

የጦር መሣሪያ የመያዝ ፈቃድ ሳይኖራቸው መሳሪያዎችን መያዝን አስመልክቶም "የጦር መሣሪያ አዋጁን በመተላለፍ በታሕሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 5 ሰዓት ላይ በልደታ ክ/ከ ወረዳ 6 በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በተደረገ ብርበራ አንድ ታጣፊ ክላሽንኮቭ መሣሪያ ከ2 ክላሽ ካዝና እና ከ60 ጥይት ጋር" መገኘቱ በክሱ ላይ ተመልክቷል።

ተከሳሹ አቶ ታየ ባቀረቡት የቃል አቤቱታ ለእሥር በተዳረጉበት ወቅት በእሳቸውና በቤተሰባቸው ላይ የሰብ ዓዊ መብቶች ጥሰቶች መድረሱንና ክሳቸውም ዘግይቶ ምመሥረቱን ተናግረዋል።

በዐቃቤ ሕግ በኩል ተያይዥ ምርመራዎችን እያከናወን እንደነበር የጠቀሰ ሲሆን፤ የዋስትና መብትን አስመልክቶ ብይን ለማሳለፍለማሳለፍ ለሚያዝያ 24 ቀን 2016 ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ ቆርጧል።


Share

Published

By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends