አንድ አዲስ የገበያ ምርምር እንዳመለከተው አምና በቦክሲንግ ቀን ሽያጭ ለሸመታ እንወጣለን ካሉት 39% አውስትራሊያውያን ዘንድሮ 42% አውስትራሊያውያን ለሸመታ እንደሚወጡ ገልጠዋል።
ይሁንና ባለፈው ዓመት ከሸመቱት $501.60 ወደ አማካይ $483.20 ዝቅ ያለ የሸመታ ዕቅድ መያዛቸው ተጠቁሟል።
ከሶስት አራተኛ በላይ (78%) ያህሉ መሸመት የፈለጉት መሠረታዊ የሆኑ ነገሮችን ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል።
የአሸማመት ዘዴያቸውን ተከትሎ ሁለት ሶስተኛ ያህሉ በኦንላይን የተቀሩት በአካል ሱቆች ተገኝቶ መሸመት እንደሆነ የገበያ ጥናቱ አመላክቷል።