በዛሬው ዕለት ቅዳሜ ሕዳር 17 ድምፅ ከሰጡ መራጮች መካከል 50 ፐርሰንቱ ቆጠራቸው ተጠናቅቋል። የሌበር ፓርቲ ራሱን ችሎ መንግሥት ለማቆም ከሚያስፈልገው 45 የምክር ቤት ወንበሮች በላይ አሸንፏል።
የሌበር ፓርቲን ሶስተኛ ዙር ምርጫ አሸናፊነት ተከትሎ ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ በቪክቶሪያ ታሪክ ለ3000 ቀናት በፕሪሚየርነት በመምራት አምስተኛው ሰው ሆነዋል።
እስከ ፋሲካ ድረስ በመሪነት ከቆዩ በቪክቶሪያ ታሪክ ለረጅም ጊዜ በሌበር ፕሪሚየርነት በመቆየት አዲስ የታሪክ ሬከርድ ያስመዘግባሉ።
እንደ ABC የምርጫ ተንታኝ አንቶኒ ግሪን ገለጣ ሌበር ፓርቲ 50 ሊብራል / ናሽልስ 23 ግሪንስ ፓርቲ 5 የምክር ቤት ወንበሮችን አሸንፈዋል።
10 የምክር ቤት ወንበሮች አሸናፊያቸው በውል አልየም።
ከዛሬው ዋነኛ የምርጫ ቀን በፊት ድምፃቸውን ከሰጡ መራጮች ውስጥ የሁለት ሚሊየን ያህሉ ቆጠራ አልተጠናቀቀም።
የምርጫውን ውጤት ተከትሎ የሊብራል / ናሽናልስ ተቃዋሚ ቡድን መሪ ማቲው ጋይ ቀደም ብለው ድል መነሳታቸውን አምነው ለወደፊቱ ቅንጅቱ ከአሁኑ ይበልጥ ተግቶ መሥራት እንዳለበት አመላክተዋል።

Victorian Opposition Leader Matthew Guy speaks to party faithful at the Liberal Party reception in Melbourne, Saturday, November 26, 2022. Credit: AAP Image

Labour party supporters cheer after the ABC had projected a Labour party win on November 26, 2022 in Melbourne, Australia. Credit: Asanka Ratnayake/Getty Images
የቪክቶሪያን ምርጫ ውጤት ተከትሎ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ፤ ለፕሪሚየር ዳን ኤል አንድሩስ "የእንኳን ደስ ያለዎት" መልዕክታቸውን በቲዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።