የቪክቶሪያ ክፍለ አገራዊ የምርጫ ጣቢያዎች በመላው ቪክቶሪያ ዛሬ ማለዳ ላይ ከ 8am አንስቶ እስከ 6pm ለመራጮች ክፍት ሆነው ውለዋል።
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መራጮች የሰጡት ድምፆች በቆጠራ ላይ ያሉ ሲሆን የተወዳዳሪ ፓርቲዎችና የግል ተመራጮች ውጤቶች በምርጫ ኮሚሽን አማካይነት እየተገለጡ ይገኛል።
እንደ ABC የምርጫ ተንታኝ አንቶኒ ግሪን ገለጣ ሌበር ፓርቲ 50 ሊብራል / ናሽልስ 23 ግሪንስ ፓርቲ 5 የምክር ቤት ወንበሮችን አሸንፈዋል።
የሌበር ፓርቲ ከምርጫ በፊት ከ88 የፓርላማ ምክር ቤት ወንበሮች 55ቱን አሸንፎ ይዞ የነበረ ሲሆን የሊብራልና ናሽናል ቅንጅት 27 ወንበሮች ነበሯቸው።
አሸናፊ ፓርቲ ራሱን ችሎ መንግሥት ለማቆም የሚያስፈልጉት ወንበሮች 45 ናቸው።
ከጥቂት ደቂቃዎች ወይም ሰዓታት በኋላ የምርጫ ኮሚሽንን ይፋ ውጤት ተከትሎ ድል የተነሱት የሊብራል/ናሽናል ፓርቲ መሪ ማቲው ጋይ እና ይድል ባለቤት የሆኑት የሌበር ፓርቲ መሪ ዳን ኤል አንድሩስ ፓርቲዎቻቸውን ወክለው ንግግር ያደርጋሉ።