የሠራዊቱን ወደ መቀሌ ዘልቆ ግዳጅ ላይ የመሠማራቱን ተግባር በዛሬው ዕለት ይፋ ያደረጉት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስት ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አቶ ሬድዋን ሁሴን ናቸው።
አቶ ሬድዋን በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቶ ታገሰ ጫፎ የተመራው ልዑክ ቡድን አባል ሆነው በትናንትናው ዕለት መቀሌ ደርሰው ተመልሰዋል።
የልዑኳን ቡድኑም ከመቀሌ መልስ የጉዟውን ሂደት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስረዳቱን የገለጡ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ለተለያዩ የፌዴራል ተቋማት ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች ተጀምረው በትግበራ ላይ ያሉ አገልግሎቶች ተፋጥነው እንዲቀጥሉ መመሪያ መስጠታቸውንም አክለው ገልጠዋል።
በመመሪያው መሠረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በነገው ዕለት አቋርጦ የነበረውን የመቀሌ በረራ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚቀጥል ሲሆን፤ ሌሎችም አገልግሎት ሰጪዎች የየድርሻ ተግባራቶቻቸውን አፋጥነው የሚቀጥሉ ይሆናል።