ይህንኑ ተከትሎ በአፍሪካ የውድድሩ ዋና አጋር መልቲቾይስ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን ሥራ ፈጣሪዎች እንዲወዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።
በአምስት የተለያዩ ምድቦች የሚካሄደውን ይህንን ዓመታዊ ሽልማት በተለይ ለአካባቢ ስሙም የሆኑና ተፈጥሮን የማይበክሉ ቢዝነሶችን የሚያንቀሳቅሱ ኢትዮጵያውያን ይህ ሽልማት ሊያመልጣቸው እንደማይገባ ተገልጿል።
ውድድሩ እስከ አንድ ሚሊዮን ፓውንድ ሽልማት የሚያስገኝ በመሆኑ ፕሮጀክቶቻቸውን ለማስፋፋትና እየተባባሰ ለመጣው የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ እንዲያበረክቱ ያግዛል ተብሏል።
መልቲቾይስ አፍሪካ እንዳሳወቀው በደቡብ አፍሪካ በተከናወነው የ2024 ውድድር ከ ጋና እና ከኬንያ ሲሆኑ የ "ግሪን አፍሪካ ዩዝ ኦርጋናዜሽን" ከ ጋና እንዲሁም "ኪፕ ኢት ኩል" የተሰኙት የአረንጓዴ ጉዳይ አቀንቃኞችና የሥራ ፈጣሪዎች አሸናፊ እንደሆኑ አስታውሷል።