የሲድኒ ከተማ ሰማይ እኩለ ለሊት ላይ በ 80,000 ፓይሮቴክኒክ ርችት ፍንዳታ በሕብረ ቀለማት ደምቆ ወገግ ይላል።
የ 8.5 ርችት ፍንዳታው ትዕይንት የሚካሔደውበሁለት ዙር ሲሆን፤ በቀዳሚነት ለቤተሰብ የሚክናወነው ትዕይንት 9pm ሲከናወን የአዲስ ዓመት ቅበላው እኩለ ለሊት ላይ በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ታግዞ ለ12 ደቂቃዎች ያህል ይካሔዳል።
የ 4.4 ሚሊየን ወጪ የተደረገበት የሜልበርን አዲስ ዓመት ቅበላ ርችት ዝግጀት ላይ 400 ሺህ ታዳሚዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።
የሜልበርን የቤተሰብ ርችት 9:30 pm ላይ ሲከናወን የአዲስ ዓመት ቅበላው እኩለ ለሊት ላይ ይከናወናል።
በመላ አገሪቱ በሚካሔዱ የርችት ትዕይንቶች ላይ የሚታደሙ አውስትራሊያውያን ሁከት ሳይፈጥሩ ጥሩ ጊዜን አሳልፈው በሰላም ወደ የቤቶቻቸው እንዲመለሱ ፖሊስ አሳስቧል፤ ሕግ በሚተላለፉቱ ላይም ተገቢው እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል።