በ2023 አውስትራሊያውያን ያለ ቪዛ መጓዝ የሚችሉባቸው አገራት እነማን ናቸው?

የአውስትራሊያ ፓስፖርት ባለቤቶች የቪዛ ማመልከቻ ማስገባት ሳያሻቸው ወደ 185 አገራት መጓዝ ይችላሉ።

Australian Passport.jpg

The Australian passport is one of the world's most desirable when it comes to visa-free travel. Credit: Getty / iStockphoto

አንኳሮች
  • በሄንሊ ፓስፖርት ሠንጠረዥ መሠረት ያለ ቪዛ ጥያቄ በመጓዝ ጃፓን ቀዳሚውን ሥፍራ የያዘች ሲሆን ዜጎቿ ወደ 193 አገራት ያለ ቪዛ መጓዝ ይችላሉ
  • አውስትራሊያ ከዓለም ስምንተኛውን ደረጃ የያዘች ሲሆን፤ ዜጎቿ ያለ ቪዛ ጥያቄ ወደ 185 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች መጓዝ ይችላሉ
  • በዓለም ላይ የአውስትራሊያ ፓስፖርት ባለቤቶችን ቪዛ ግድ የሚሉ 42 አገራት አሉ
ሠንጠረዡ የተቀመረው መቀመጫው ሎንዶን በሆነው የፍልሰት ሙዋዕለ ንዋይ አማካሪ ድርጅት ሄንሊ እና ሽርካዎቹ ሲሆን፤ የዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ዳታን ከቪዛ ነፃ የሆኑ 199 አገራት ፓስፖርቶችንና 227 መዳረሻዎችን በማነፃፀር ነው።

በ 2023 የሲንጋፖርና ደቡብ ኮሪያ ፓስፖርቶች ከዓለም ሁለተኛ በጣሙን ብርቱ ሲሆኑ፤ ጀርመንና ስፔይን በሶስተኝነት ተከትለዋቸዋል።
The most powerful passport.jpg
Japan topped the latest Henley Passport Index. Credit: SBS News
አፍጋኒስታን ኢራቅና ሶሪያን አስከትላ ከሠንጠረዡ ታች ወርዳ ትገኛለች።
The least powerful paspports.jpg
The Henley Passport Index ranks the Afghan passport as the least powerful. Credit: SBS News
አውስትራሊያውን ያለ ቪዛ መጓዝ የሚችሉባቸው አገራት

የአውስትራሊያ ፓስፖርት ተጠቃሚዎች ያለ አንዳች ቪዛ ጥየቃ፣ የቪዛ ፈቃድ ወይም ከመዳረሻቸው እንደደረሱ በኤሌክትሮኒክ ቪዛ የሚዘልቁባቸው 185 አገራት አሉ።

አውስትራሊያውያን ከፖርቱጋል እስከ ፖላንድ፣ ከእንግሊዝ እስከ ዩክሬይንን አካትቶ በአርባ ዘጠኝ የአውሮፓ አገራት ለመጓጓዝ የመግቢያ ቪዛ አያሻቸውም።

እንዲሁም በኦሺንያ ኒውዚላንድ፣ ፊጂ፣ የፈረንሳይ ፖሎኒዥያ አክሎ፣ በተመሳሳዩም በካሪቢያን ባርቤዶስ፣ ካይማን ደሴቶችና ጃማይካን ጨምሮ የመግቢያ ቪዛ ግድ አይሰኙም።

በአኅጉረ አሜሪካዎች አርጀንቲና፣ ብራዚልና ሜክሲኮን ጨምሮ ወደ አሥራ ዘጠኝ አገራት እንዲሁም ቦትስዋና፣ ሞሮኮና ቱኒዚያን አክሎ ወደ 12 አገራት ለመዝለቅ የመግቢያ ቪዛ አያሻቸውም።

አውስትራሊያውያን ሆንግ ኮንግ፣ ማሌዥያና ፊሊፒንስን አክትቶ 10 የእስያ አገራትን፤ እንዲሁም እሥራኤልንና ኳታርን ጨምሮ ስድስት የመካከለኛው ምሥራቅ አገራትን ያለ ቪዛ መጎብኘት ይችላሉ።

ካምቦዲያ፣ ግብፅ፣ ሊባኖስ፣ ፓራጓይና ሳሞኣ አውስትራሊያውያን የመግቢያ ቪዛ ወይም የጎብኚዎች ፈቃድ መዳረሻቸው ላይ እንደደረሱ ከሚጠየቁባቸው 40 አገራት ተጠቃሽ ናቸው።

እንደ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ካናዳ፣ ፓኪስታንና ሽሪላንካ ሲደርሱ የኤሌክትሮኒክ ቪዛ ይጠየቃሉ።

ለአውስትርሊያውን ቪዛ የሚያስፈልጓቸው አገራት

የአውስትራሊያ ቪዛ ባለቤቶች በቅድሚያ አውስትራሊያን ለቅቀው ከመጓዛቸው በፊት ቪዛ መያዝ የሚያስፈልጋቸው ወይም ቅድመ ይሁንታ ከመንግሥት አግኝተው ወደ አቀኑበት አገር እንደደረሱ ቪዛ የሚጠየቁባቸው 42 መዳረሻዎች አሉ።

ከገሚስ በላዩ ጋና፣ ኬንያና ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ የአፍሪካ አገራት ናቸው።

አውስትራሊያውያን ወደ መዳረሻቸው ከመዝለቃቸው በፊት የግድ ቪዛ ማግኘት የሚገባቸው በካሪቢያን ኩባ፣ በኦሺኒያ ናሩ ሲሆኑ፤ እስያ ውስጥ አፍጋኒስታን፣ ቻይናና ሰሜን ኮሪያን አካትቶ 10 አገራት ቪዛን ግድ ይላሉ።

ወደ አውሮፓ ማቅናት የሚሹ ለአዘርባጃን፣ ሩስያ ወይም ቱርክ፣ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሶሪያና የመን፣ ወደ አሜሪካዎች ቺሊ እና ሱሪናም የመግቢያ ቪዛ ያስፈልጋቸዋል።

ለአስትራሊያውያን በጣኑን ዝነኛ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች

እንደ አውስትራሊያ ስታቲስቲክ ቢሮ ወቅታዊ ዳታ የአውስትራሊያ ነዋሪዎች በጣሙን ዝነኛ ዓለም አቀፍ መዳረሻ ኢንዶኔዥያ ናት።

ለአውስትራሊያውያን በሁለተኛ ደረጃ የጉብኝት ሥፍራነት የሚገኙት ኒውዝላንድና ዩናይትድ ስቴትስ ሲሆኑ፤ በሶስተኛ ደረጃ ከ10 ዋነኛ መዳረሻዎች ውስጥ እንግሊዝ፣ ሲንጋፖር፣ ሕንድ፣ ፊጂ፣ ታይላንድ፣ ጣሊያንና ቬይትናም ናቸው።

ከእነዚህ መዳረሻ አገራት ውስጥ አውስትራሊያውያንን የመግቢያ ቪዛ የሚጠይቁ አገራት ሕንድና ቬይትናም ብቻ ናቸው።






Share
Published 12 January 2023 8:48pm
By Kassahun Seboqa Negewo, Amy Hall
Source: SBS

Share this with family and friends