የኢትዮጵያ መንግሥትና የሕወሓት ጦር ገዲብ አዛዦች ዳግም ናይሮቢ ላይ ታደሙ

ስብሰባው የጋራ ቁጥጥር፣ ማጣራትና አከባበር ዘዴ ውል ማጣቀሻ ላይ ተወያይቶ ከማጠቃለያ ደርሷል። እንዲሁም፤ የትጥቅ ፍቺ፣ ብተናና ዳግም ቅልቅል ላይም ተነጋግሯል።

Commanders.jpg

The second meeting of the Senior Commanders of the Federal Democratic Republic of Ethiopia (FDRE) and the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) on December 22, 2022, in Nairobi, Kenya. Credit: AUC

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በተሰየሙ የሰላም ልዑካን ቡድን እየተመራ ያለው የኢትዮጵያ መንግሥትና የሕወሓት ተደራዳሪዎች መካከል ቀጥሎ ያለው ቋሚ ከግጭት ዕቀባ ስምምነት ሂደት ትግበራ ክትትል ስብሰባ ዳግም ዲሴምበር 22/ ታሕሳስ 23 ናይሮቢ ከተማ ተካሂዷል።

ስብሰባው የጋራ ቁጥጥር፣ ማጣራትና አከባበር ዘዴ ውል ማጣቀሻ ላይ ተወያይቶ ከማጠቃለያ ደርሷል። እንዲሁም፤ የትጥቅ ፍቺ፣ ብተናና ዳግም ቅልቅል ላይም ተነጋግሯል።

የገዲብ አዛዦቹ ስብሰባ የተካሔደው በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚደንት በሚመራው ልዑክ ቡድን ሲሆን፤ በዕለቱም የልዑካን ቡድን አባላቱ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚደንት ዶ/ር ፉምዚሌ ምላምቦ ጉካ አማካይነት ነው።





Share

Published

By Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends