Latest

የአውስትራሊያ የወረርሽኝ አስቸኳይ ግብረ ምላሽ ዛሬ አብቅቷል፤ ለውጦቹን እነሆ

አንድ አዲስ የጥናት ሞዴል እንደሚያመልክተው ከሆነ ደቡብ አውስትራሊያ ውስጥ የኮቪድ ወረሽኝ በዲሴምበር መጀመሪያ ግድም የሚያሻቅብ ሲሆን፤ የከፋ እንደማይሆን ይጠበቃል። ደቡብ አውስትራሊያ በገና በዓል አካባቢ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሕሙማን ሆስፒታል ሊተኙባት እንደሚችሉ ተገምቷል።

AUSTRALIAN DAILY LIFE

Workers and pedestrians are seen during lunch time at Circular Quay on a sunny day under the canopy of jacaranda trees in Sydney. (file) Source: AAP / BRENDAN ESPOSITO/AAPIMAGE

አንኳሮች
  • አንድ አዲስ የአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ ጥናት እንደሚያሳየው ከ10 አውስትራሊያውያን አንዳቸው ለረጅም ጊዘ በኮቪድ ታምመዋል
  • የዓለም ጤና ድርጅት በኮቪድ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር በ10 ፐርሰንት ቀንሷል
  • የሞደርና ባይቫለንት ክትባት ለአውስትራሊያውያን ዝግጁ ነው
  • የምዕራብ ሲድኒ ነዋሪዎች የኮቪድ ወረርሽኝ ገደብ በተጣለበት ወቅት ዘር ተኮር ልዩነት እንደተደረገባቸው ተሰምቷቸዋል፤ ሪፖርት
ግዴታ ተጥሎበት የነበረው የኮቪድ -19 ወሸባ በመላው አውስትራሊያ ዛሬ ኦክቶበር 14 / ጥቅምት 4 አብቅቷል።

ከወሸባ የመግባት ግዴታ ማክተም ጋር ተያይዞ የወረርሽኝ ሕክምና ፈቃድ ክፍያም አብሮ አክትሟል። ይሁንና በአረጋዊያን ክብካቤ፣ የግብረ አካል ጉዳተኞች ክብካቤ፣ የአቦርጂናል የጤና ክብካቤና የሆስፒታል ክብካቤ መስኮችን አያካትትም።

የኒው ሳውዝ ዌይልስ ጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ ተጋላጭነት ባለበት ሁኔታ ውስጥ የሚገኙና በኮቪድ-19 ተጠቂ የሆኑ ሠራተኞች ወደ ሥራ ገበታቸው መመለስ የሚችሉት ለሰባት ቀናት ወሸባ ከገቡና ከሕመሙ ምልክቶችም ነፃ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ መሆኑን አስታውቋል።

በተወሰኑ ክፍለ አገራትና ክፍለ ግዛቶች በቫይረሱ የተሰጡ ሰዎች የRAT ምርመራ ውጤቶቻቸውን ሪፖርት የማድረግ ግዴታ ፀንቶ አለ።

ተጋላጭነታቸው ከፍ ባለባቸው ሥፍራዎች የፊት ጭምብሎችን ከማጥለቅና የጤና ክብካቤ ሠራተኞች የክትባት ግዴታ በስተቀር አብዛኞዎቹ ተጥለው የነበሩ የኮቪድ-19 ድንጋጌዎች ተነስተዋል።
አንድ አዲስ የአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ ከ10 አውስትራሊያውያን አንዳቸው ለረጅም ጊዜ በኮቪድ የታመሙ ናቸው።

የጥናቱ ዋና መሪ ፕሮፌሰር ኒኮላስ ባይድል ተደጋጋሚ ምልክቶች የታዩባቸው ወይም ለረጅም ጊዜ ኮቪድ ያጠቃቸው ሰዎች ጤንነታቸው በብርቱ ያሽቆለቆለ መሆኑን በሪፖርታቸው አመላክተዋል።

የዋናውን ኮቪድ ቫይረስና ኦሚክሮን BA.1 ንን ዒላማ ያደረገው የሞደርና ባይቫለንት ክትባት ለአውስትራሊያውን ዝግጁ ሆኗል።

ይሁንና አንድ የዓለም ጤና ድርጅት ተጠባቢዎች ቡድን በአሁኑ ወቅት ያለው ዳታ ባይቫለንት ክትባትን ለመጠቀም የሚያስችል ምክረ ሃሳብ ለመስጠት በቂ ሆኖ እንዳላገኘው ገልጧል።

ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው ባለፈው ወር እምብዛም የማጠናከሪያ ክትባት ተከታቢ ባለመኖሩ 20 ፐርሰንት የኮቪድ ክትባት ከጥቅም ውጪ ተደርጓል።

ከማጠናከሪያ ክትባት አኳያ በዓለም የጤና ድርጅት ከ15 እስከ 40 ፐርሰንት ጥቅም ላይ ያለመዋላቸው ተቀባይነት ያለው ሲሆን፤ የአውስትራሊያ ከዚያ ያነሰ ነው።
በአውስትራሊያ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲና የተባበሩት ሠራተኞች ማኅበር የተሰናዳ አንድ ሪፖርት እንዳመለከተው በአብዛኛው የመድብለ ባሕል ማሕበርሰብ አባላት በሚኖሩባቸው የምዕራብ ሲድኒ ክፍለ ከተሞች ከሲድኒ ባለ ፀጋዎች መኖሪያ ጋር ሲነፃፀር የኮቪድ ወረርሽኝን ተከትሎ የተጣለው ገደብ በምዕራብ ሲድኒ ነዋሪዎች ዘንድ ዘር ተኮር ሆኖ ተሰምቷቸዋል።

ሪፖርቱ "የምዕራብ ሲድኒ ነዋሪዎችና ሌሎች የአካባቢ መንግሥታዊ አስተዳደሮች ከተቀረው ይየሲዲኒ አካባቢ በተለይ የተጣሉባቸው ብርቱ የአካላዊ እንቅስቃሴ ገደብና የምሽት ሰዓት ዕላፊ ጫና የታከለበት ነበር" ብሏል።

ምዕራብ አውስትራሊያ በመንግሥት የሚካሔዱትን የክትባት ክሊኒኮች እየቀነሰ ነው። ሆኖም፤ ክትባቶች በጠቅላላ ሕኪሞችና መድኃኒት ቤቶች ይሰጣሉ።

አንድ አዲስ የጥናት ሞዴል እንደሚያመልክተው ከሆነ ደቡብ አውስትራሊያ ውስጥ የኮቪድ ወረሽኝ በዲሴምበር መጀመሪያ ግድም የሚያሻቅብ ሲሆን፤ የከፋ እንደማይሆን ይጠበቃል።

ደቡብ አውስትራሊያ በገና በዓል አካባቢ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሕሙማን ሆስፒታል ሊተኙባት እንደሚችሉ ተገምቷል።
የኮቪድ-19 መነሻ ከእንሰሳት ወደ ሰው ተላላፊ በመሆን ሊሆን እንደሚችል አተያዩን ገልጧል።

በተጨማሪም ግብረ ኃይሉ ኮቪድ-19 ከላቦራቶሪ ስለመመንጨቱ "ተጣሪና ወይም ተአማኒ መረጃ" እንዳላገኘ አመልክቷል።

የዓለም ጤና ድርጅት ወቅታዊ ሪፖርት እንዳመልከተው ኦክቶበር 9 ባበቃው ሳምንት ውስጥ የቫይረስ ተጠቂዎችና ሞት ቁጥር በ10 ፐርሰንት ቀንሷል።

ጀርመን፣ ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ጣሊያን በሳምንቱ ውስጥ በቫይረስ መስፋፋት ከፍተኛውን ሥፍራ ይዘው ተገኝተዋል።

Find a Long COVID clinic

Find a COVID-19 testing clinic
Register your RAT results here, if you're positive
Before you head overseas, Here is some help understanding Read all COVID-19 information in your language on the

Share
Published 14 October 2022 3:16pm
By Kassahun Seboqa Negewo, SBS-ALC content
Source: SBS


Share this with family and friends