ቀድሞ የነበሩ የጤና ጠንቆች የኮሮና ቫይረስን ሊያባብሱ ይችላሉ
ቀድሞውኑ የነበረ የጤና ችግር ያላባቸው ስዎች በኮቪድ- 19 ከተያዙ ጤናቸው ለአደጋ ይጋለጣል፡፡
በተለይ የልብ ፤ የስኳር ፤ የደም ብዛት እና የአስም በሽታ ያለባቸውን መጥቀስ ይቻላል፡፡ቫይረሱ የሳንባን ክፍል በማጥቃት እብጠት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ በ በኮቪድ- 19 ከተያዙት ህመምተኞች መካከል 70% ያህሉ ቀድሞውኑ የነበረ የጤና ችግር ያላባቸው ስዎች ናቸው፡፡
በኮቪድ- 19 ዋናዎቹ እና አደገኛ የጤና ችግሮች የሚባሉት ፦ ስር የሰደደ የሳንባ ህመም ፤ አስም ፤ የልብ ህመም ፤ የስኳር በሽታ ፤ የጉበት እና የኩላሊት በሽታዎች ሲሆኑ እንዲሁም ሌሎች ህክምናዎች እና መድሃኒቶች የመከላከል አቅምን ያዳክማሉ፡፡እንደ ካንሰር እና ከነቀላ በኋላ የሚደረጉ ህክምናዎችን ያጠቃልላል፡፡
አስም
አስም የመተንፍሻ አካል ችግር ሲሆን መነሾውም በመተንፈሻ አካላት ላይ በሚፈጠር መቆጣት እና ማበጥ ነው፡፡ምልክቶቹም ሳል ፤ ለመተንፈስ መቸገር ፤ የደረት መወጠር ፤ ትንፋሽ ቁርጥ ቁርጥ ማለት ናቸው፡፡በአሁን ሰአት 11 % የሚሆኑት አውስትራሊያውያን በአስም እንደተቁ ይገመታል፡፡ የነባር ዜጎች ከሊሎች አውስትራሊያውያን ጋር ሲነጻጸሩ አብላጫውን ቁጥር ይሸፍናሉ፡፡የአስም ህመም የመተንፈሻ አካላትን ሊረብሹ በሚችሉ በማናቸውም ነገሮች ሊቀሰቀስ ይችላል፡፡ ኮቪድ- 19 የመተንፈሻ አካላትን እንደሚያጠቃ ሁሉ አስም ያለባቸው ሰዎች ከፍተኛ ጥንቃቄን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ሌሎች የሳንባ ህመሞች
በአውስትራልያ ከአስም ቀጥሎ በከፍተና ሁኔታ ተላላፊ የሚባሉት የሳንባ ህመሞች የሚከተሉት ናቸው ፦ አስቤስቶሲስ ( በአስቤስቶ የሚመጣ የሳንባ ህመም ) ብሮንካይተስ (የሳንባ ምች ) ሲስቲክ ፋይብሮሲስ ፤ ኢምፈሲምያ ( የመተንፈስ ችግር ) የሳንባ ካንሰር ፤ ፕሉራል ኢፊውዥን ፤ፕሉሪስይ ፤ ሪስፓይራቶሪ ሲሊኮሲስ ፤ የሳንባ ነቀርሳ ይገኙበታል፡፡
የልብ ህመም
የአለም አቀፍ ምርምሮች እንደሚጠቁሙት የልብ ህመም ያለባቸው ስዎች በኮቪድ- 19 የመሞት እድላቸው ከተቀረው ህብረተሰብ ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ነው፡፡ ይህም የመያዝ አቅማቸው ከፍተኛ መሆን ብቻ ሳይሆን በሌሎች በሽታዎች የመያዛቸው እድላቸውም ከፍተና ስለሚሆን ነው፡፡ኮቪድ- 19 ፈጣን የሆነ እብጠትን በልብ ጡንቻዎች ላይ በመፍጠር እንዲቆስል በማድረግ የልብ ምት ማቆምን ያስከትላል፡፡
ጤናማ የአኗኗር ዘዴ እጅግ በጣም ያስፈልጋል ፦ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማድረግ ፤የተመጣጠነ ምግብን መመገብ ፤ውሃን መጠጣት ፤ በቂ እንቅልፍን መተኛት ጠቃሚ ነው፡፡እንደ የአለም አቀፍ የጤና ድርጅት ምክር ከሆነ በሳምንት ውስጥ 150 ደቂቃ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ ወይም 75 ደቂቃ ከከፍተኛ እስክ ጥልቅ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በቤት ውስጥ ማድረግ እንደሚገባ ይገባል፡፡
የስኳር በሽታ
የስኳር በሽታ ታማሚዎች ተጨማሪ የጤና ችግሮችን ሊጋፈጡ ይችላሉ፡፡እንደ Diabetes Australia ምክር ከሆነ የጉንፋን ክትባትን መውሰድ ፤ ህመም በሚኖር ጊዜ ምን መደረግ እንዳለበት ቀድሞ ማቀድ ፤በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን መቆጣጠር ያስፈልጋል፡፡ የስኳር ህሙማን ከሌሎች ህመሙ ያልዛቸው ጋር ሲነጻጸሩ በጉንፋን የመያዝ እና የመተንፈሻ አካል ችግር የመጋፈጥ እድላቸው ከፈተኛ ነው፡፡በርካታ ታይፕ 2 የስኳር ህሙማን ከመጠን ባላይ ውፍረት ያላቸው በመሆናቸው ለተለያዩ ቁስለቶች የተጋለጡ ናቸው፡፡
የጉበት በሽታ
በሄፐታይተስ ቢ ውይም ሲ ወይም በሌላ የጉበት በሽታ የተያዙ እንደ አጠቃላይ ማህበረሰቡ ተመሳሳይ የሆኑ ጥንቃዎችን ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ነቅቶ በመጠባበቅ የሚነገሩትን ማሳሰቢያዎች በመከተል ራሳችውብ ኮቪድ- 19 መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡የጉበት በሽተኞች የኢንፍሉዌንዛ እና የሳንባ ምች ክትባትን እንዲያደርጉ ይመከራሉ፡፡
የኩላሊት በሽታ
የኩላሊት በሽታ ያለባቸው ስዎች የጉንፋን በሽታን መጠንቀቅ ያለባቸው ሲሆን በኮሮና ቫይረስ የመያዝ እና ተያያዝዥ በሆኑ ችግሮች የመጋለጣቸው እድልም ከፍተኛ ነው፡፡ ህመምተኞቹ ደህና ካልህኑ ኮቪድ-19 ከሰውነት ውስጥ ያለውን ውህ በማድረቅ ለቁስለት ይዳርጋቸዋል፡፡
የካንሰር ህክምና
ህሙማን የካንሰር ህክምናን በሚያደጉ ጊዜ የሰውነት የመከላከያ አቅማቸው እጅግ የሚዳከም ሲሆን በተከታታይም የጤና ባለሙያዎችን ምክር ሆነ የጥንቃቄ ማሳሰቢያን በመከተል ተጨማሪ ቁስለት እንዳይከሰት መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል፡፡አስፈላጊ ከሆነ ጉዞ ውጭ በተቻለ መጠን ሁሉ ከቤታቸው እንዳይወጡ ይመከራል፡፡
በአውስትራሊያ የሚኖሩ ዜጎች 1. 5 ሜትር ርቀትን መጠበቅ አለባቸው፡፡ መሰባሰብን በተመለከተም የክልሉን ገደብ መጠን መመልከት ያስፈልጋል፡፡
የኮሮና ቫይረስ ምርመራ በአሁን ሰአት በሰፊው ይደረጋል፡፡የብርድ ወይም ጉንፋን ምልክቶችን ካሳዮ ሃኪምዎ ጋር በመደወል ምርመራን እንዲያደርጉ መጠየቅ የሚችሉ ሲሆን ወይም coronavirus Health Information Hotline on 1800 020 080 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
The federal Government’s coronavirus tracing app COVIDSafe በይፋ ስለወጣ በስልክዎ ላይ ይጫኑ፡፡
ኤስ ቢ ኤስ ለአውስትራሊያውያን መድብለ ባህል ማህበረሰብ አዳዲስ ኮቪድ- 19 መረጃዎችን በትጋት ያደርሳል፡፡ ዜናዎች እና መረጃዎች በ63 ቋንቋዎች ይገኛሉ ከ