- በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ዳታ መሠረት በመላው ዓለም በኮቪድ-19 ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ይፋዊ ቁጥር 6 ሚሊየን ደረሰ
- በመስኩ ጠበብት ዘንድ ግና በተለይም ከታዳጊ አገራት የግንዛቤና ሪፖርት አቀራረብ አኳያ ቁጥሩ ከዚህም የላቀ እንደሚሆን ይታመናል። ቲኪ ፓንግ ከብሔራዊ የሲንጋፖር ዩኒቨርሲቲ የሉላዊ ጤና ጎብኚ ፕሮፌሰር "ትክክለኛው የሟቾች ቁጥር 21 ሚሊየን አካባቢ" እንደሚሆን ተናግረዋል።
- ምዕራብ አውስትራሊያ ውስጥ ልጃቸው በኮቪድ -19 የተያዘ ወላጆች ወይም ተከባካቢዎች እንደቅርብ ንኪኪ ያለው ግለሰብ ተቆጥረው አብረው ወሸባ እንዳይገቡ ተደረገ።
- የተቀሩትም የቤተሰብ አባላት የሕመም ምልክቶቻቸውን ልብ ብለው በመከታተል ወደ ሥራ ወይም ወደ ትምህርት ቤት መሔድ ይችላሉ።
- ምዕራብ አውስትራሊያ ሆስፒታል ተኝንተው ያሉ ሕሙማንን በመጠየቂያ ሰዓታት አንድ ጎብኚ በየተራ እንዲጠይቃቸው ተፈቅዷል።
- ሌላ ጎብኚም በተመሳሳይ ቀን በተለያየ የመጠየቂያ ሰዓታት በየሁለት ሰዓት ፈረቃ መጠየቅ ይችላል። ለ የተለዩ ሁኔታዎች ይመቻቻሉ።
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 9,017 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የአምስት ሰዎች ሕይወት አልፏል። ሆስፒታል ከሚገኙት 1,066 ሕመማን 43 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
ቪክቶሪያ ውስጥ 5,645 በቫይረስ ሲጠቁ፤ 2 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 227 ሕመማን 29 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች 7 በአየር መተንፈሻ መሳሪያ እየተረዱ ይገኛሉ።
ኩዊንስላንድ 3,677 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ አንድ ግለሰብ ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርጓል። ሆስፒታል ከሚገኙት 267 ሕመማን 20 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
ታዝማኒያ 784 ሰዎች በቫይረስ ሲጠቁ፤ ሆስፒታል ከሚገኙት 21 ሕሙማን መካክል 5 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል ይገኛሉ።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 553 ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 2ሕመማን 3 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል ይገኛል።
Find a COVID-19 testing clinic
Register your RAT results here, if you're positive