የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ - ባለፉት 24 ሰዓታት የ93 አውትራሊያውያን ሕይወቶች በኮቪድ-19 ተቀጠፉ

*** ትናንት በተካሔደው 65ኛ የብሔራዊ ካቢኔ ስብሰባ ላይ የክፍለ አገራት መሪዎች የሆስፒታልና ፅኑዕ ሕመምተኞች ክፍል ታካሚዎች ቁጥር እየቀነሰ መሆኑን ገለጡ።

COVID-19 update

Paramedics tending to their ambulance outside St. Vincent hospital in Melbourne. Source: AAP

  • አውስትራሊያ ውስጥ 93 ሰዎች ሕይወታቸውን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጡ። ወረርሽኙ ከተከሰተ ወዲህ በ24 ሰዓታት ውስጥ የዚህ ዓይነት ከፍተኛ የሞት ቁጥር ሲመዘገብ ይህ የመጀመሪያ ክስተት ነው።
  • የ16 እና 17 ዓመት ታዳጊ ወጣቶች የኮቪድ-19 መከላከያ ሶስተኛ ዙር ፋይዘር ክትባት እንዲከተቡ የአውስትራሊያ ክትባት አማካሪ ቡድን ጊዜያዊ ይሁንታ ቸረ። ቀደም ለሶስተኛ ዙር ክትባት መመዘኛን ያሟሉ የነበሩት ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ ያሉ ናቸው።
  • የቪክቶሪያና ኒው ሳውዝ ዌይልስ ፖለቲከኞችን ጥሪ ተከትሎ የጤና ተጠባቢዎች ለሶስት ዙር ክትባቶች የ "ሙሉ ክትባትነት" ትርጓሜ ለመስጠት  ከውሳኔ ላይ አልደረሱም። 
  • የኖርዘርን ቴሪቶሪ ነባር ዜጎች ተሟጋች ድርጅቶች የኮቪድD-19 ተዛማችነት ለመግታት በመላው ማዕከላዊ አውስትራሊያ አስቸኳይ ገደብ እንዲጣል ዋና ሚኒስትሩን በአቤቱታ ደብዳቤ ጠየቁ።
  • ትናንት በተካሔደው 65ኛ የብሔራዊ ካቢኔ ስብሰባ ላይ የክፍለ አገራት መሪዎች የሆስፒታልና ፅኑዕ ሕመምተኞች ክፍል ታካሚዎች ቁጥር እየቀነሰ መሆኑን ገለጡ። 
  • በበርካታ ክፍለ አገራት የተማሪዎች በአካል ወደ መማሪያ ክፍሎቻቸው የመመለስ ዕቅድ በሂደት ላይ ሲሆን፤ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ለሁሉም ተማሪዎች የሚመለሱባቸው ትምህርት ቤቶች ፈጣን አንቲጄን መመርመሪያዎች፣ አውቶቡሱችና ባቡሮች መደልደላቸው ተገለጠ። 
  • ቪክቶሪያ ውስጥ ከወዲሁ 2 ሚሊየን ፈጣን አንቲጄን መመርመሪያ ለመንግሥት፣ ካቶሊክና የግለ ትምህርት ቤቶች ታድሏል። ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ከመመለሳቸው በፊትም 6 ሚሊየን ፈጣን መመርመሪያዎች እንደሚሰራጩ ይጠበቃል። 
  • ይሁንና ኩዊንስላንድ ውስጥ ወላጆች፣ አስተማሪዎችና ተማሪዎች የመንግሥት የተማሪዎች መመለሻ ዕቅድ ይፋ እስኪሆን ድረስ እየጠበቁ ይገኛሉ። 
  • ኩዊንስላንድ 18 ነዋሪዎቿ ሕይወታቸውን እንዳጡና 12ቱ በአረጋውያን መጠወሪያ ውስጥ የነበሩ መሆናቸውን አስመዝግባለች።

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 13,333  ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የ35 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፤ ሆስፒታል ከሚገኙት 2,737 ሕመማን 189 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ። 

ቪክቶሪያ ውስጥ 12,755 በቫይረስ ሲጠቁ፤ 39 ሕይወታቸውን አጥተዋል።  ሆስፒታል ከሚገኙት 988 ሕመማን 114 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ። 

 ኩዊንስላንድ 9,974 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ 18 ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 818 ሕመማን 54 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ። 

ታዝማኒያ  584 ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 19 ሕመማን 1 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛል።

ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ግብረ ምላሽ የሰፈሩትን በቋንቋዎ ለመረዳት ይህን ይጫኑ .

 


የተለያዩ ከፍለ አገራት የፈጣን አንቲጄን ምርመራ መመዝገቢያ ቅጾች፤

 


ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤

ጉዞ

 የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ 

የገንዘብ እርዳታ

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤  


በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለ-ባሕል ጤና አገልግሎት የተተረጎሙ መረጃዎችን እዚህ ያግኙ


የክፍለ አገራት ምርመራ ክሊኒኮች

 
 
 

 






Share
Published 28 January 2022 5:09pm
By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends