- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 67 ፐርሰንት ነዋሪዎች የመጀመሪያ ዙር ክትባት ተከተቡ
- የቪክቶሪያ ኮቪድ-19 ተጋላጨነት ሥፍራዎች ከ 1,000 ደረሱ
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ የኮሮናቫይረስ ገደብ እስከ ሴፕቴምበር 17 ተራዘመ
- ደቡብ አውስትራሊያ በኖርዘርን ቴሪቶሪ እና ኩዊንስላንድ ላይ ጥላ የነበረውን ገደብ አነሳች
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,164 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ 796ቱ የምዕራባዊና ደቡባዊ ሲድኒ ነዋሪዎች ናቸው። ሶስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ዋና የጤና መኮንን ዶ/ር ኬሪ ቻንት የጊልፎርድ፣ ሜሪላንድስ፣ ኦበርን፣ ግሪነኤከር፣ ባንክስታውንና ብላክታውን ነዋሪዎች እንዲመረመሩ አሳሰቡ።
የጤና ሚኒስትር ብራድ ሃዛርድ በቂ የፋይዘር ክትባት ስለሌለ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ አስትራዜኔካ ክትባትን እንዲከተቡ ምክረ ሃሳብ ቸሩ።
ሰኞ ዕለት የደቡብ ምዕራብ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪ የሆነ የመጀመሪያው አንድ የነባር ዜጎች ሰው ሕይወት በኮቪድ-19 ማለፉ ተነግሯል።
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 76 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። 31ዱ ቫይረሱ ከተስፋፋባቸው ሥፍራዎች አይደሉም።
እንደራሴ አንድሩስ በነገው ዕለት የሚረግቡ ገደቦችን ለማስታወቅ ዕቅድ ይዘዋል። "ትክክለኛው ክትባት ሊከተቡት የሚችሉት ክትባት ነው" በማለትም በርካታ የአስትራዜኔካ ክትባት መኖሩንና ሰዎችም እንዲከተቡት አበረታተዋል።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 13 ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል። ስምንቱ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።
የካንብራ አዲሱ የኮቪድ-19 መጠነ ሰፊ የክትባት ክሊኒክ የአውስትራሊያ ስፖርት ኢንስቲትዩት ውስጥ ሴፕቴምበር 3 ይከፈታል። ከሐሙስ ሴፕቴምበር 2 ከቀትር በኋላ 5pm ጀምሮ እስከ ሴፕቴምበር 17 ድረስ የሚቆዩ አዲስ ገደቦች ተጥለዋል .
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ደቡብ አውስትራሊያ ከደቡብ ምሥራቅ ኩዊንስላንድ እና ከካትሪን ኖርዘርን ቴሪቶሪ ተጉዘው ለሚመጡ ጥላቸው የነበሩትን ገደቦች ሁሉ አነሳች
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤