ጉዞ
- ሙሉ ክትባት የተከተቡ በኒው ሳውዝ ዌይልስ፣ ቪክቶሪያና የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ የሚገኙ የአውስትራሊያ ዜጎችና ቋሚ ነዋሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ልዩ ፈቃድ ሳይጠይቁ ከአገር መውጣትና ወደ አገር ሲመለሱም ወሸባ መግባት ግድ አይሰኙም።
- የአውስትራሊያ ዜጎችና ቋሚ ነዋሪ ወላጆችም ከዛሬ ጀምሮ ወደ አውስትራሊያ በ በኩል አመልክተው መምጣት ይችላሉ።
- ሙሉ ክትባት የተከተቡ የሲድኒና የሪጂናል ኒው ሳውዝ ዌይልስ ነዋሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሲድኒና ወደ ሪጂናል ኒው ሳውዝ ዌይልስ መጓዝ ይችላሉ።
- የኒው ሳውዝ ዌይልስ የመግቢያ ፈቃድ በወሰን አካባቢ ባሉ ነዋሪዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ተፈፃሚነት አይኖረውም።
- ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ሙሉ ክትባት ያልተከተቡ የቪክቶሪያ ነዋሪዎች ወደ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ለሽርሽር መሔድ አይችሉም።
- ሙሉ ክትባት የተከተቡ ካንብራውያውያን ወደ ኒው ሳውዝ ዌይልስና ቪክቶሪያ መጓዝ ይችላሉ።
የክትባት አሰጣጥ
- የኮቪድ-19 ሁለተኛ ዙር ክትባት ከተከተቡ ስድስት ወር ያለፋቸው የኒው ሳውዝ ዌይልስ ጎልማሶች የሶስተኛ ዙር ማጠናከሪያ ክትባት በአካባቢያቸው ከሚገኙ መድኃኒት ቤቶች፣ ወይም ጠቅላላ ሐኪማቸው ዘንድ አለያም ወደ ክትባት ማዕከላት በመሔድ መከተብ ይችላሉ።
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ
- ቪክቶሪያ ውስጥ 1,471 በኮሮናቫይረስ ሲጠቁ አራት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 135 በቫይረስ ሲጠቁ አራት ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል።