- የመጀመሪያ ዙር ክትባት የተከተቡ አውስትራሊያውያን ቁጥር 90 ፐርሰንት አለፈ።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን የፌዴራል መንግሥቱ በቪክቶሪያ ወረርሽኝ ድንጋጌዎች ጣልቃ እንደማይገባ አስታወቁ።
- የኩዊንስላንድ ፕሪሚየር አናስታዥያ ፓለሼይ የ12 ክፍል መልቀቂያ የጨረሱ ተማሪዎችን ዓመታዊ ፓርቲ እንደማይሰርዙ ገልጠው፤ ሆኖም ምንጩ ያልታወቀ ቫይረስ ከተከሰተ ግና ብርቱ ውሳኔ ለማሳለፍ እንደማያመነቱ አሳሰቡ።
- ታዝማኒያ ዕድሜያቸው ከ 16-24 ያሉና ክትባት የተከተቡ በቡድን የመሰብሰብና የዳንስ ፌስቲቫሎች ላይ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ሰዎችን አስመልክቶ የገደቦች ክለሳ እያደረገች ነው።
- የምዕራብ አውስትራሊያ ክትባት ኮሚሽነር ክሪስ ዳውሰን የክትባት ደረጃው ዝቅተኛ የሆነባቸው ነባር ዜጎች መኖሪያ ሥፍራ ላሉ የማኅበረሰብ አረጋውያን በግል ተማፅኖ አቀረቡ።
- ከኖቬምበር 15 ጀምሮ ሲድኒ ውስጥ በብርቱ አስፈላጊ ያልሆኑ የቀዶ ሕክምና ግልጋሎቶች በሙሉ አቅም ይሰጣል።
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ቪክቶሪያ ውስጥ 1,115 በቫይረስ ሲጠቁ፤ ዘጠኝ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 286 ነዋሪዎቿ በቫይረስ መጠቃታቸውንና የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን አስታወቀች።
ኩዊንስላንድ ውስት ሁለት ሰዎች በቫይረስ ሲያዙ፤ የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 15 ነዋሪዎች ተጠቅተዋል።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤