የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ፤ "አውስትራሊያ ከዓለም በእጅጉ ከተከተቡ አገራት አንዷ ናት" ጠ/ሚ ስኮት ሞሪሰን

*** ቪክቶሪያ በነገው ዕለት ተጨማሪ ገደቦችን ልታነሳዋዜማ ላይ ባለችበት ወቅት 25 ነዋሪዎቿ በኮቪድ-19 ሳቢያ ሕይወታቸውን አጡ

COVID-19 update

Speaking from Parliament House, Canberra, PM Scott Morrison said that Australians will be able to travel overseas from next Monday. Source: AAP

  • ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ሶስተኛ ዙር የማጠናከሪያ ክትባት ከኖቬምበር 8 ጀምሮ መሰጠት እንደሚጀምር አስታወቁ
  • ቪክቶሪያ በወረርሽኝ ሳቢያ ከፍተኛ ዕለታዊ የሟቾች ቁጥር አስመዘገበች
  • ኩዊንስላንድ በተሰጣቸው ቀነ ገደብ ሳይከተቡ የቀሩ 150 የፖሊስ ሠራዊት አባላትን ከሥራቸው ተገልለው እንዲቆዩ ወሰነች

 ቪክቶሪያ

ቪክቶሪያ ውስጥ 1,923 ነዋሪዎች በ25 ዕለታዊ የኮቪድ ሟቾች ቁጥርን አስመዘገበ ተጠቁ፤ 25 ዕለታዊ የኮቪድ ሟቾች ቁጥርን አስመዘገበች።

ይህ የሆነውም ክለ አገሪቱ በነገው ዕለት ተጨማሪ ገደቦች ለማንሳት በመሰናዶ ላይ ሳለች ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ለሟች ቤተሰቦች የተሰማቸውን ጥልቅ ኃዘን በመግለጽ “ይህ የወረርሽኙን አስከፊ ዕውነታ ልብ የሚያሰኝ አስደማሚ ሁነት ነው" ብለዋል። 

የቪክቶሪያ ጤና ዲፓርትመንት ከኮቪድ-19 ክትባት ራሳቸውን ያገለሉ ሰዎች የአውስትራሊያ ክትባት ምዝገባ ማረጋገጫቸውን የሚያቀርቡብት ጊዜ አሁን መሆኑን አሳሰበ።

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ   

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
 ኒው ሳውዝ ዌይልስ 293 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ሁለት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። 

ከዳርሊንግኸርስት የአካል ማጠንከሪያ ሥፍራ ጋር በተያያዘ 15 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ።

ከኦክቶበር 18 እስከ 23 ወይም 25 ባሉት ጊዜያት ውስጥ የአካል ማጠንከሪያ ሥፍራው ላይ የተገኙ ሰዎች ምርመራ እንዲያካሂዱና ከቫይረስ ነፃ ለመሆናቸው ማረጋገጫ እስኪያገኙም ድረስ ራሳቸውን አግልለው እንዲቆዩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። 

የደንበኞች ግልጋሎት ሚኒስትር ቪክቶር ዶሚኒሎ ከዓርብ ጀምሮ ተጋላጭ ሥፍራዎች ላይ የተገኙ ሰዎች በሰርቪስ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ኧፕ አማካይነት ማሳሰቢያ እንደሚደርሳቸው ገለጡ። 

አቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ  

ኩዊንስላንድ

ኦክቶበር 4 ቀነ ገደብ መከተብ ሲገባቸው ያልተከተቡ 150 ያህል የኩዊንስላንድ ፖሊስ ሠራዊት አባላት ከሥራቸው ተገልለው እንዲቆዩ ተወሰነ። 

ኩዊንስላንድ ውስጥ በዛሬው ዕለት አንድም ግለሰብ በቫይረስ አልተያዘም። 

የክትባት ቀነ ቀጠሮ ለማስያዝ አሁኑኑ ይህን ይጫኑ  

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ

  • ከኖቬምበር 8 ጀምሮ የመጀመሪያ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ ዙር ማጠናከሪያ ከትባቶች በሁሉም የአውስትራሊያ መድኃኒት ቤቶች ይገኛል።
  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ስምንት ነዋሪዎች በቫይረስ ተያዙ።
  • ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ሶስት አራተኛ አውስትራሊያውያን ሙሉ ክትባት የተከተቡ መሆናቸውን ገለጡ።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 
 

 

 

 

 


Share
Published 28 October 2021 6:01pm
By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends