ከዲሲምበር 1 ጀምሮ ሙሉ ክትባት የተከተቡና መመዘኛን ያሟሉ ባለ ቪዛዎች የልዩ ፈቃድ ማመልከቻ ሳያስገቡ ወደ አውስትራሊያ መዝለቅ ይችላሉ።
መመዘኛን ያሟሉ ባለ ቪዛዎች ባለ ሙያ ሠራተኞችና ዓለም አቀፍ ተማሪዎች፣ የሽርሽርና ጊዜያዊ ሠራተኞች፣ የሰብዓዊ ቪዛና ጊዜያዊ ቪዛ ያላቸው ስደተኞችን ያካትታል። ወደ አውስትራሊያ ከመዝለቃቸው በፊትም ሙሉ ክትባት መከተብ ይኖርባቸዋል፣ ከትባት የተከተቡበትን ማስረጃ ሊያቀርቡ ይገባል፣ ጉዞ ከመጀመራቸው ሶስት ቀናት ቀደም ብለው ከቫይረስ ነፃ መሆናቸውን የሚያመለክት የPCR ምርመራ ውጤት ሊኖራቸው ግድ ይላል።
በተጨማሪም ከዲሴምበር 1 ጀምሮ አውስትራሊያ በጃፓንና ኮሪያ ያሉ ዜጎችን ልዩ ፈቃድ ሳያሻቸው ትቀበላለች።
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ቪክቶሪያ ውስጥ 1,029 በቫይረስ ሲጠቁ፤ ሶስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 180 ነዋሪዎቿ በቫይረስ መጠቃታቸውንና የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን አስታወቀች።
ኖርዘን ቴሪቶሪ ውስጥ ሁለት ሰዎች በቫይረስ ተይዘዋል። ካትሪን ላይ ተጥሎ ያለው ገደብ እስከ ኖቬምበር 24 ከምሽቱ 6pm ድረስ ተራዝሟል።
በቫይረስ ተይዘዋል።
ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤
ጉዞ
የገንዘብ እርዳታ
ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤