አውስትራሊያ ውስጥ 30 ሰዎች በኮቪድ-19 ሳቢያ ሕይወታቸው ማለፉ ተመዘገበ።
ከሟቾቹ ውስጥ 16ቱ ከኒው ሳውዝ ዌይልስ፣ ሰባት ከኩዊንስላንድ፣ አራት ከቪክቶሪያ፣ ሶስት ከደቡብ አውስትራሊያ ሲሆኑ፤ ምዕራብ አውስትራሊያ በበኩሏ ሶስት ቀደም ሲል ሕይወታቸው ያለፈ ግለሰቦችን አስመዝግባለች።
የአውስትራሊያ ዋና የሕክምና መኮንን ፕሮፌሰር ፖል ኬሊ የኮቪድ-19 ዕለታዊ የሟቾች ቁጥሮችን ሪፖርት ማድረግ እንዲያበቃ አሳሰበዋል።
በሌላ በኩል የኮቪድ-19 ግብረ ኃይል አዛዥ ሌተና ጄኔራል ጆን ፍሬዌን ከአንድ የሴኔት ኮሚቴ ዘንድ ቀርበው እንደተናገሩት ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በታች ያሉ አውስትራሊያውያን የሶስተኛ ዙር ክትባቶችን ከመከተብ ያዘገሙ መሆናቸውን ተናግረዋል።
አክለውም፤ ቀደም ሲል በነበሩት የቫይረስ ዝርያዎች ላይ አድሮባቸው የነበረው ዓይነት ፍራቻ በኦሚክሮን ላይ እንዳላደረባቸው ገልጠዋል።
ሰዎች በኮቪድ-19 መያዝ አለመያዛቸውን በሳል ድምፅ የሚያሳውቀው ResApp በኩዊንስላንድ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ ሲቸረው፤ የአውስትራሊያ ስቶክ ኤክስቼንጅም የባሕር መዝግቡ ላይ አስፍሮታል።
ኩባንያው በ741 ሕሙማን ላይ ዩናይትድ ስቴትስ እና ሕንድ ውስጥ ባካሔደው ቅድመ ክሊኒካዊ ሙከራ 92 ፐርሰንት ኮቪድ-19 ሕሙማን የሳል ድምፆች ለይቶ በትክክል በቫይረሱ የተጠቁ መሆኑን አስታውቋል። ውጤቱም ከፈጣን አንቲጄን መመርመሪያ የላቀ መሆኑን ገልጧል።
ኩባንያው ResApp አውስትራሊያ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲውል ከጤና ባለስልጣናት ጋር ለመነጋገር ዕቅድ መያዙን አመላክቷል።
ትንናት ረቡዕ ቻይና ወረርሽኙ ከሁለት ዓመት በፊት ከተከሰተ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ከ20,000 በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን አስታወቀች።
የአውስትራሊያ ዕለታዊ ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ - ኤፕሪል 7, 2022
ኒው ሳውዝ ዌይልስ፤ 22,255 ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል፣ ሆስፒታል ከሚገኙት1,437 ሕሙማን ውስጥ 48ቱ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ሲገኙ፤ 16 ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ቪክቶሪያ፤ 12,314 በቫይረስ ተይዘዋል፤ ሆስፒታል ከሚገኙ 283 ሕሙማን ውስጥ 12 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ሲገኙ አራት ለሞት ተዳርገዋል።
ኩዊንስላንድ፤ 10,984 በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ሆስፒታል ከሚገኙ 444 ሕሙማን ውስጥ 17 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ሲገኙ ሰባት ለሕልፈተ ሕይወት በቅተዋል።
ምዕራብ አውስትራሊያ፤ 7,998 በቫይረስ ተይዘዋል፤ ሆስፒታል ከሚገኙ 256 ሕሙማን ውስጥ ስምንት በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ሲገኙ ቀደም ሲል ሕይወታቸው ያለፈ ሶስት ሰዎች ተመዝግበዋል።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ፤ 1,094 በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ሆስፒታል ከሚገኙ 49 ሕሙማን ውስጥ ሶስት በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ሲገኙ አንድም ሕይወቱ ያለፈ ሰው አልተመዘገበም።
ታዝማኒያ፤ 2,365 በቫይረስ ተይዘዋል፤ ሆስፒታል ከሚገኙ 43 ሕሙማን ውስጥ አንድ ግለሰብ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል ሲገኝ አንድም ለሕልፈተ ሕይወት የተዳረገ ሰው የለም።
ኖርዘርን ቴሪቶሪ፤ 513 በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ሆስፒታል ከሚገኙ 24 ሕሙማን ውስጥ አንድ ግለሰብ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል ሲገኝ አንድም ለሕልፈተ ሕይወት የተዳረገ ሰው የለም።
ደቡብ አውስትራሊያ፤ 6,091 በቫይረስ ተይዘዋል፤ ሆስፒታል ከሚገኙ 210 ሕሙማን ውስጥ 12 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ሲገኙ ሕይወታቸው ያለፈ ሶስት ሰዎች ተመዝግበዋል።
Find a COVID-19 testing clinic
Register your RAT results here, if you're positive