ፋይዘር ዕድሜያቸው ከ5 እስከ 11 ላሉ ልጆች ክትባት መስጠት እንዲችል የፈዋሽ ቁሶች አስተዳደር ይሁንታን ለማግኘት ማመልከቻ ማስገባቱን የፌዴራል ጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት አስታወቁ።
በቀጣይነትም ከአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን ዕድሜያቸው ይሁንታ እንደተገኘም ዕድሜያቸው ከ5 እስከ 11 ላሉ ልጆች ክትባት መስጠት ይጀመራል።
አቶ ሃንት በመጪዎቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ሙሉ ክትባት የተከተቡ አውስትራሊያውያን ቁጥር 80 ፐርሰንት እንደሚያልፍ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ኩዊንስላንድ በምትገኘው ጉንዲዊንዲ ከተማ ኮሮናቫይረስ በመከሰቱ የምርመራ ጣቢያዎች ተቋቁመዋል። ይሁንና ከተማይቱ ላይ ገደቦች አልተጣሉም።
ከዛሬ ጀምሮ የሚካሔደውን የዲዋሊ ክብረ በዓል ተከትሎ የኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕል ጤና ኮሚሽን አገልግሎት የተወሰኑ ምክረ ሃሳቦችን ሰጥቷል።
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ

Source: NSW Health
- ቪክቶሪያ ውስጥ 1,247 ነዋሪዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ዘጠኝ ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል።
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ 308 በቫይረስ ተጠቅተዋል፤ ዘጠኝ ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል።
- ኩዊንስላንድ ውስጥ ሶስት ሰዎች በቫይረስ ተጠቁ።
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ 13 ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል።
የክትባት አሰጣጥ
የማጠናከሪያ ሶስተኛ ዙር ክትባት ኖርዘር ቴሪቶሪ ውስጥ ከሰኞ ኖቬምበር 8 ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል፤ ሆኖም ግዴታ አይሆንም።