- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ አብዛኛዎቹ በቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ዕድሜያቸው ከ40 በታች ነው
- የቪክቶሪያ እንደራሴ ከፍ ላለ የምርመራ መጠን ጥሪ አቀረቡ
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ አሥራ ሰባት ሰዎች በቫይረስ ተጠቁ
- ኖርዘርን ቴሪቶሪ ውስጥ በቫይረስ የተጠቃ አልተመዘገበም
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 452 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ 50 ያህሉ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው። የአራት ሰዎች ሕይወት አልፏል። ሰባ አምስት ፐርሰንት ያህል አዲስ በቫይረስ ከተጠቁ ሰዎች ውስጥ ዕድሜያቸው ከ40 በታች ነው። የአንዲት ዕድሜያቸው በ70ዎቹ የነበረና ክትባት ያልወሰዱ አረጋዊት ሕይወት አልፏል።
የሌኖክስ ሄድ ነዋሪዎች የኮቪድ ተዛማችነት ዌስትዎተር ውስጥ መከሰትን ተከትሎ ምርመራ እንዲያደረጉ ተነግሯል።
እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን ዕድሜያቸው ከ70 በላይ ያሉ እንዲከተቡ ልዩ ጥሪ አደረጉ።
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 24 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። ሶስቱ ቀደም ሲል ወረርሽኙ ተዛምቶባቸው ከነበሩ ሥፍራዎች አይደሉም። አሥሩ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።
እንደራሴ ዳንኤል አንድሩስ ፖርት ፊሊፕ እና ቤይሳይድን ጨምሮ የሴይንት ኪልዳ አካባቢ ክፍለ ከተሞች የምርመራ መጠናቸውን ከፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ።
የመመርመሪያ ጣቢያዎችን ማወቅ ከፈለጉ ይህን ይጫኑ በአቅራቢያዎ የሚገኙ የክትባት ማዕከላትን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ .
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 17 ሰዎች በቫይረስ መያዛቸውን አመልክታለች፤ ጠቅላላ ካንብራ ውስጥ በቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 45 ደርሷል። በአሁኑ ወቅት የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ ውስጥ ወደ 100 የተቃረቡ የተጋላጭነት ሥፍራዎች አሉ .
- ኖርዘርን ቴሪቶሪ ውስጥ ትናንት ከተካሄዱት 1,846 ምርመራዎች በቫይረስ የተጠቃ አንድም ሰው አልተገኘም።
- ኩዊንስላንድ ወሸባ ገብቶ ያለ አንድ ግለሰብ በቫይረስ መጠቃቱን አስመዘገበች።
ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤