በቪክቶሪያና ኒው ሳውዝ ዌይልስ መካከል ያሉ ወሰኖች ሙሉ በሙሉ ተከፈቱ። ተለያይተው የቆዩ ቤተሰቦች ዳግም ተገናኝተዋል፤ በዓለም ካሉ የተጨናንቀ የአየር መስመር አንዱ በሆነው የበረራ መንገድ መንገድ በጢያራ መጓጓዝ ይችላሉ።
የብሔራዊ ካቢኔው ከአምስት ሳምንታት በኋላ የኮቪድ-19 ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ይነጋገራል አጀንዳዎቹም ዓለም አቀፍ ድንበሮችን መክፈትና የሕፃናት ክትባቶችን የሚመለከት ነው።
የእንግሊዝ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሳይንቲስቶች በኮቪድ-19 ሳቢያ ለሳምባና ሞት በእጥፍ ተጋላጭ የሚያደርግ ጂን አገኙ። ጂኑ የደቡብ እስያ ዝርያ ባላቸው ሰዎች ዘንድ በዝቶ የሚታይ ነው።
የኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ
ቪክቶሪያ ውስጥ 1,343 ሰዎች በቫይረስ ተጠቁ፤ 10 ለሕልፈተ ሕይወት ተዳረጉ።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 249 ነዋሪዎቿ በኮቪድ-19 መያዛቸውንና ሶስት ሕይወታቸውን ማጣታቸውን አስመዘገበች።
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤