- ኒው ሳውዝ ዌይልስ፣ ቪክቶሪያ እና ኩዊንስላንድን አካትቶ ባለፉት 24 ሰዓታት የ22 ሰዎች ሕይወት በኮቪድ 19 ሳቢያ አልፏል። ይህም ከወር ከፍ ባለ ጊዜ ውስጥ ዝቅተኛው የሞት ቁጥር ነው።
- ቪክቶሪያ ከሶስት ሳምንታት በኋላ የጤና ሥርዓቷ ማሳሰቢያ የነበረውን የኮድ ቡናማ ማስጠንቀቂያዋን አነሳች። ግብር ላይ ውሎ የነበረው የኦሚክሮን ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ ወርኃ ጃኑዋሪ ውስጥ ነበር።
- የቪክቶሪያ ክፍለ አገር የጤና ሚኒስትር ማርቲን ፎሊ ከዕለተ ዓርብ ጀምሮ የቡናማ ኮድ ማስጠንቀቂያ እንደሚያከትም በመንግሥት በኩል ሙሉ እምነት መኖሩን ጠቁመው፤ ሆኖም ሆስፒታሎች "በጣም በጣም ጥድፊያ የሚበዛባቸው" ሆነው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
- በአሁኑ ወቅት 465 ሰዎች የሆስፒታል ሕክምንና እየተከታተሉ ሲሆን፤ ጃኑዋሪ 17 ከተመዘገበው ከፍተኛው 1,229 የኮቪድ - 19 ሕሙማን ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛው ነው።
- በቪክቶሪያ ጤና ዲፓርትመንት ዳታ መሠረት ክትባት ያልተከተቡ ሰዎች በኮቪድ ሲጠቁ ለፅኑ ሕሙማን ክፍል መዳረግ ሶስተኛ ዙር ክትባት ከተከተቡት ጋር ሲነፃፃር 34 እጅ እጥፍ ነው።
- የኩዊንስላንድ ጤና ሚኒስትር ኢቬት ዳት ትምህርት ቤቶች ከተከፈቱ የመጀመሪያው ሳምንት ውስጥ መጠነ ሰፊ የቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር አለመመዝገቡን ገለጡ።
- የኩዊንስላንድ መንግሥት የኮቪድ -19 አዲስ ተጠቂዎች፣ የሆስፒታል ሕሙማንና የሟቾች ቁጥር እየቀነሰ መሔዱን ከቀጠለ ዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚገታ አስተወቀ።
- ከአንድ አሠት ዓመት ወዲህ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ነርሶች ነገ ማክሰኞ ጠዋት ከ 7am ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ ያደርጋሉ።
- በዕለቱም አንድ ነርስ መከባከብ የሚችለው የበሽተኛ ቁጥር መጠን በአግባቡ እንዲሻሻልና የደመወዝ ጭማሪ እንዲደረግ ጥሪያቸውን ዳግም ያሰማሉ።
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 6,184 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የ14 ሰዎች ሕይወት አልፏል። ሆስፒታል ከሚገኙት 1,649 ሕመማን 100 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
ቪክቶሪያ ውስጥ 7,104 በቫይረስ ሲጠቁ፤ 2 ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 465 ሕመማን በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች 18 በአየር መተንፈሻ መሳሪያ እየተረዱ ይገኛሉ።
ኩዊንስላንድ 3,750 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ 6 ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 514 ሕመማን 41 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ።
ታዝማኒያ 408 ሰዎች በቫይረስ ሲጠቁ፤ ሆስፒታል ከሚገኙት 12 ሕሙማን መካክል አንድ ግለሰብ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል ይገኛል።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 375 ነዋሪዎች በቫይረስ ተይዘዋል።
የተለያዩ ከፍለ አገራት የፈጣን አንቲጄን ምርመራ መመዝገቢያ ቅጾች፤
ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤
ጉዞ
የገንዘብ እርዳታ
ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤
- ከ60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ዜናዎችና መረጃዎች ከ
- የክፍለ አገርዎ ረብ ያላቸው መምሪያዎች , , , , , , .
- ስለ ኮቪድ-19 መረጃ በቋንቋዎ