- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ባርናቢ ጆይስ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል። የጤናቸው ሁኔታ ወደ አውስትራሊያ ለመመለስ እስከሚያስችላቸው ድረስ እዚያው ወሸባ ገብተው ይቆያሉ።
- ኩዊንስላንድ ውስጥ ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ ሆኖ ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 80 ፐርሰንት ደረሰ።

Source: S.Morrison
- ኩዊንስላንድ እና ቪክቶሪያ ውስጥ በኦሚክሮን ቫይረስ የተያዙ የመጀመሪያ ሰዎች በተገኙበት ማግስት፤ የጤና ተጠባቢዎች ቫይረሱ አውስትራሊያ ውስጥ ከፍ ያለ ጫና እንደሚያሳድር አሳሰቡ።
- ሲድኒ ውስጥ በአንድ መጠጥ ቤት በተካሄደ የምሽት ዝግጅት ላይ የተገኙ 44 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። ሆኖም ግለሰቦቹ የተጠቁት በአዲሱ ኦሚክሮን መሆን አለመሆኑ አልተገለጠም።
- ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ስምንት ሰዎች በኦሚክሮን ተያዙ፤ ክፍለ አገሪቱ ውስጥ በድምሩ 42 ሰዎች በአዲሱ ቫይረስ ተጠቅተዋል።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን የቴኒስ ኮከቡ ኖቫክ ጆኮቪች አውስትራሊያ ኦፕን ላይ ተገኝቶ ለመጫወት 'እንደ ማንኛውም ሰው' የክትባት ደንቦችን ማክበር እንዳለበት ገለጡ።
ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤
ቪክቶሪያ ውስጥ 1,232 በቫይረስ ሲጠቁ፤ ዘጠኝ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 420 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የአንድ ግለሰብ ሕይወት አልፏል።
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ አራት ነዋሪዎች በቫይረስ ተጠቅተዋል።
ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤
ጉዞ
የገንዘብ እርዳታ
ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤