- ኔው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ናረ
- ሜልበርን ውስጥ የኮቪድ-19 ተጋላጭነት ሥፍራዎች ከ450 በላይ ደረሱ
- ኩዊንስላንድ የማኅበረሰብ ተጋቦት አልባ ሆና አደረች
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ በቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ሰባት ደረሱ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 466 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ 68 ያህሉ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው። የአራት ሰዎች ሕይወት አልፏል።
የኒው ሳውዝ ዌይልስ ገደብ ድንጋጌን ከፖሊስ ጋር ከሰኞ 16 ጀምሮ በጋራ ለማስከበር 500 የአውስትራሊያ መከላከያ አባላት መታከላቸውን እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን አስታወቁ።
ከሲድኒ ወጥተው መጓዝ የሚፈልጉ የመዘዋወሪያ ፈቃድ ለማግኘት የማመልከት ግዴታ አለባቸው . ለሁሉም የሲድኒ ነዋሪዎች ከቤታቸው ወጥተው የመንቀሳቀስ ገደብ ከ10 ኪሎ ሜትር ወደ 5 ኪሎ ሜትር ዝቅ አለ።
ከሰኞ ኦገስት 16 ጀምሮ በ12 የአካባቢ መንግሥት ነዋሪዎች ከቤታቸው መውጣት የሚችሉት ለአካላዊ እንቅስቃሴና ልጆችን ለመከባከብ ሲሆን፤ ከቤት ውጪ ላለ መዝናኛ የተፈቀደ አይደለም። ለብቻቸው የሚኖሩ ላጤዎች ከወዲሁ የላጤ ወዳጃቸውን ሊያስመዘግቡ ይገባል .
የሕዝብ ጤና ትዕዛዞችን በሚጥሱ ሰዎች ላይ የሚጣለው ቅጣት ወደ $5,000 ከፍ ብሏል።
ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 21 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል። ሶስቱ ቀደም ሲል ወረርሽኙ ተዛምቶባቸው ከነበሩ ሥፍራዎች አይደሉም። አሥሩ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።
የሜልበርን ቻድስተን የገበያ ማዕከል በኮቪድ-19 ተጋላጭነት ሥፍራ ተመዝግቧል። በአሁኑ ወቅት ሜልበርን ውስጥ ሃይፖይንት የገበያ ማዕከልንና በርካታ አፓርትመንቶችን ጨምሮ ከ450 በላይ የተጋላጭነት ሥፍራዎች አሉ
ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
- ኩዊንስላንድ ስድስት ሰዎች በቫይረስ ተጠቅተውባታል። ሁሉም ወረርሽኙ ተዛምቶባቸው ከነበሩ ሥፍራዎችና ወሸባ ገብተው የነበሩ ናቸው።
- የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ አንድ ሰው በቫይረስ የተያዘባት ሲሆን በጠቅላላው ሰባት ሰዎች ተጠቅተዋል።
ወሸባ፣ ጉዞ፣ የክሊኒክ ምርመራና የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤
ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።
- ዜናዎችና መረጃዎችን ከ 60 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመጎብኘት ይመልከቱ።
- ስለ ሚኖሩበት ክፍለ አገር ጠቃሚ መረጃዎችን ከፈለጉ፤ , , , , , , ይጫኑ።
- መረጃዎችን በቋንቋዎ ለማግኘት ይህን ይጫኑ .
በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤
የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤
የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤