የኮቪድ - 19 ወቅታዊ መረጃ፤ የፌዴራል መንግሥቱ ከኦክቶበር ጀምሮ የክትባት ፓስፖርት ግብር ላይ እንደሚውል አስታወቀ

*** ከሺፐርተን በስተቀር ሪጂናል ቪክቶሪያ ላይ ተጥሎ የነበረ ገደብ ሊነሳ ነው

COVID-19 update

A member of the public scans a QR code to check into a seafood store in Bankstown, Sydney, Wednesday, September 8, 2021 Source: AAP

  • በኒው ሳውዝ ዌይልስ መካከለኛ ሰሜን የባሕር ጠረፍ የተለያዩ ሥፍራዎች ኮሮናቫይረስ መከሰቱ ተስተዋለ
 

  • የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የክትባት ቀጠሮ በስልክ እንዲይዙ ተነገረ

ኒው ሳውዝ ዌይልስ
ኒው ሳውዝ ዌይልስ 1,480 ነዋሪዎቿ በቫይረስ ተጠቁ። ዘጠኝ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ህይወታቸው ካለፈው ዘጠኝ ሰዎች ውስጥ ሰባቱ ክትባት ያልተከተቡ ናቸው።

ቦኒ ሂልስ አካባቢ የቫይረስ ክስተት ሲመዘገብ፤ በግሌብ፣ ሬድፈርንና ማሪክቪል ክፍለ ከተሞች እየናረ የመጣው በቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አስግቷል። የአካባቢው ነዋሪዎች በአስቸኳይ እንዲከተቡ የኒው ሳውዝ ዌይልስ ጤና መሥሪያ ቤት አሳስቧል።

እንደራሴ ግላዲስ በርጂክሊያን 75 ፐርሰንት ነዋሪዎች የመጀመሪያ ዙር 45 ፐርሰንት የሁለተኛ ዙር ክትባት መከተባቸውን ገልጠዋል።

ዛሬውኑ የክትባት ቀጠሮዎን ለማስያዝ ይህን ይጫኑ  

ቪክቶሪያ
ቪክቶሪያ በዛሬው ዕለት 221 ነዋሪዎቿ በኮሮናቫይረስ ተጠቅተዋል፤ 98ቱ ከታወቁ ቫይረሱ የተስፋፋባቸው ሥፍራዎች ናቸው። 

ከሴፕቴምበር 9 እኩለ ለሊት አንስቶ ከሺፐርተን በስተቀር በሪጂናል ቪክቶሪያ ላይ ተጥለው የነበሩ ገደቦች ይነሳሉ  

በሚቀጠለው ሳምንት 10,000 የአስትራዜኔካ ክትባቶች ለተከታቢዎች ዝግጁ ሆነው አሉ። 

በአቅራቢያዎ የሚገኝ የክትባት ማዕከልን ማወቅ ካሹ ይህን ይጫኑ  near 

የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ
የአውስትራሊያ ካፒታል ቴሪቶሪ 20 ነዋሪዎች ተጠቅተዋል፤ 11 ያህሉ የማኅበረሰብ ተጋቦት ናቸው።

የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከሴፕቴምበር 17 በፊት የክትባት ቀጠሮአቸውን አስይዘው እንዲጨርሱ ማሳሰቢያ ተሰጠ  ተከታቢዎች በስልክ ቁጥር  ደውለው ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ።

ለክትባትዎን ቀጠሮ ለማስያዝ ይህን ይጫኑ  

ያለፉት 24 ሰዓታት በአውስትራሊያ ዙሪያ
  • የፌዴራል መንግሥቱ ለዓለም አቀፍ መንገደኞች የክትባት ፓስፖርት ግብር ላይ እንደሚውል አስታወቀ፤ ሆኖም በአውስትራሊያ ክፍለ አገራት መካከል ያሉ ወሰኖች መች ክፍት እንደሚሆኑ አልገለጠም። 
የወሸባና ምርመራ መመዘኛዎች የሚከናወኑትና ግብር ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት በክፍለ አገራት መንግሥታት ነው፤

ወደ ባሕር ማዶ መጓዝ ካሹ፤ ከገደብ ነፃ የሚያደርግዎትን ይሁንታ ለማግኘት ማመልክቻዎን በኦላይን ማቅረብ ይኖርብዎታል። አውስትራሊያን ለቅቆ ለመውጣት ስለሚያስችሉ ሁኔታዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ይጫኑ . ዓለም አቀፍ በረራዎችን በተመለከተ በመንግሥት በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች በ  ድረ ገጽ ላይ ይሰፍራሉ።





በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለባሕላዊ ጤና ኮሙኒኬሽን ግልጋሎቶች የተተረጎሙ መረጃን ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን ይጫኑ፤

የምርመራ ክሊኒኮች በየክፍለ አገራት፤


 
 

የወረርሽኝ አደጋ ክፍያ መረጃ በየክፍለ አገራት፤

 
 
 

 

 


Share
Published 8 September 2021 5:17pm
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends