የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ - የሶስተኛ ዙር ክትባትን ለማካተት የሙሉ ክትባት ትርጓሜ አጠራር ተለወጠ

*** የፌዴራል ጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት በአዲሱ የክትባት ምክረ ሃሳብ መሠረት ሶስተኛ ዙር ክትባት ለአረጋውያን ክብካቤ ሠራተኞች ግዴታ መሆኑን አስታወቁ።

COVID-19 update

Federal Health Minister Greg Hunt. Source: AAP

  • የአውስትራሊያ የክትባት ቴክኒካዊ አማካሪ ቡድን "ሙሉ ክትባት" ከሚሉ ቃላት ወደ "ወቅታዊ" ክትባት አጠራር የማምራት ተገቢነትን አስመልክቶ ምክረ ሃሳብ ቸረ። 
  • ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ የሆኑ አውስትራሊያውያን ወደ "ወቅታዊ" ክትባት ደረጃ ለመሸጋገር የሶስተኛ ዙር ኮቪድ-19 ክትባትን መከተብ ግድ ሲላቸው፤ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ሆኖ ሁለት ዙር ክትባቶችን የተከተቡ በ "ወቅታዊ" ክትባት ተከታቢነት ደረጃ ይመደባሉ። 
  • የሙሉ ክትባት ደረጃ አጠራር ለአገር ውስጥ የኮቪድ ፖሊሲ የሚውል ሲሆን በዓለም አቀፍ የድንበር ከፈታ ዕቅድ ውስጥ የተካተተ አይደለም። 
  • የተሻሻለው ምክረ ሃሳብ ከወርሃ ማርች መጨረሻ ጀምሮ ግብር ላይ ይውላል። 
  • የአውስትራሊያ ዓለም አቀፍ ድንበሮች ከፌብሪዋሪ 21 ጀምሮ ክፍት ሲሆኑ፤ የባሕር ማዶ ቱሪስቶች ወደ አውስትራሊያ ለመዝለቅ መከተብ የሚያሻቸው የሁለት ዙር ክትባቶችን ብቻ ነው ።
  • የፌዴራል ጤና ሚኒስትር ግሬግ ሃንት በአዲሱ የክትባት ምክረ ሃሳብ መሠረት ሶስተኛ ዙር ክትባት ለአረጋውያን ክብካቤ ሠራተኞች ግዴታ መሆኑን ተናግረዋል። 
  • ዛሬ ዓርብ ኒው ሳውዝ ዌይልስ፣ ቪክቶሪያ፣ ኩዊንስላንድ እና ደቡብ አውስትራሊያ በኮቪድ-19 ሳቢያ የ48 ነዋሪዎቻቸው ሕይወት መቀጠፉን አስመዘገቡ። 
  • ደቡብ አውስትራሊያ ውስጥ በቡና ቤቶች፣ ክለቦችና ምግብ ቤቶች ላይ ተጥለው የነበሩ የመስተንግዶ መጠን ገደቦች ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ይነሳሉ። 

ኮቪድ-19 ስታቲስቲክስ፤

ኒው ሳውዝ ዌይልስ 8,950 ነዋሪዎቿ በቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፤ የ19 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፤ ሆስፒታል ከሚገኙት 1,716 ሕመማን 108 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ። 

ቪክቶሪያ ውስጥ 8,521  በቫይረስ ሲጠቁ፤ 13 ሕይወታቸውን አጥተዋል።  ሆስፒታል ከሚገኙት 553 ሕመማን 82 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ። 

ኩዊንስላንድ 5,977 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ 14 ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 554 ሕመማን 45 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ። 

ታዝማኒያ 552 ሰዎች በቫይረስ ሲጠቁ፤ ሆስፒታል ከሚገኙት 16 ሕሙማን መካክል አንድ ግለሰብ በፅኑዕ ሕሙማን ክፍል ይገኛል።

ደቡብ አውስትራሊያ 1,445 ነዋሪዎች በቫይረስ ሲያዙ፣ ሁለት ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል። ሆስፒታል ከሚገኙት 210 ሕመማን 16 በፅኑዕ ሕሙማን ክፍሎች ይገኛሉ። 

ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ግብረ ምላሽ የሰፈሩትን በቋንቋዎ ለመረዳት ይህን ይጫኑ .

 


የተለያዩ ከፍለ አገራት የፈጣን አንቲጄን ምርመራ መመዝገቢያ ቅጾች፤

 


ወሸባና ገደቦች ክፍለ አገር በክፍለ አገር፤

ጉዞ

 የኮቪድ-19 እና የጉዞ መረጃ 

የገንዘብ እርዳታ

ሙሉ ክትባት የተከተቡ ነዋሪዎች ቁጥር 70 እና 80 ፐርሰንት በደረሰባቸው ክፍለ ኣገራት የኮቪድ-19 Disaster Payment ይለወጣል፤  


በኒው ሳውዝ ዌይልስ መድብለ-ባሕል ጤና አገልግሎት የተተረጎሙ መረጃዎችን እዚህ ያግኙ


የክፍለ አገራት ምርመራ ክሊኒኮች

 
 
 

 






Share
Published 11 February 2022 6:02pm
By SBS/ALC Content
Presented by Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends